መቱ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን አስመረቀ

ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎቹን ያስመረቀን በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች በመደበኛና በተከታታይ ፕሮግራሞች ስያስተምራቸው የነበረውን ነው፡፡ እነዚህ ተመራቂ ተማሪዎች 1152 ሲሆኑ ከነዚህም 373 ሴቶች ናቸው፡፡ በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት ክብር ዶ/ር ሙላቱ ተሸመ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ ክብሪት ወ/ሮ አስተር ማሞ በሚኒስተር ማዕረግ የመለስ ዘናዊ አካዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንትና የመቱ ዪኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ ጨምሮ ሌሎች የቦርድ አባላት ፣ የዩኒቨርሲቲው አመራር፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንገዶች፣ የተመራቂ ተማሪዎች ቤተሰቦች ናቸው፡፡ በዕለቱም ዶ/ር ታደሰ ሀብታሙ የመቱ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ባደረጉት ንግግር ዩኒቨርሲቲው በ2009 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአቅም ግንባታ፣ መሰረተ ልማት፣ በተማሪዎች መጠነ መውደቅ፣ በማስፋፊያ ግንባታዎች ከባለፉት ዓመታት በተሻለ መልኩ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በሚቀጥለው ዓመትም እነዚህን ስረዎች በማስቀጠልና የተገኙትን ተሞክሮዎች በመቀመር የተሻለ ስራ ለመስራት ማቀዱን ገልጸዋል፡፡
በመቀጠልም ክቡር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንትና የዕለቱ የክብር ዕንግዳ ባደረጉት ንግግር የሀገሪቱ 2ናውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ለማሳካት ተመራቂ ተማሪዎች ባገኙት ዕውቀትና ክህሎት ህዝባቸውንና ሀገራቸውን እንዲያለግሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በተጨማሪም መቱ ዩኒቨርሲቲ በሚያደርጋቸው የመማር ማስተማር፣ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት እየሰራ ያለው ስራ የሚያስመሰግን መሆኑን ተናገረው በቀጣይ የማህበረሰቡን ጤና ለመጠበቅ በሚደረገው ጥረት ውስጥ አጠናክረው መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በዕለቱ በትምህርታቸው አብላጫ ውጤት ያስመዘገቡ ተመራቂ ተማሪዎች ከዕለቱ የክብር ዕንግዳ ከክቡር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዕጅ ተቀብለዋል፡፡

News_Image: