የድህረ ምረቃ ትምህርት እየተማራችሁ ላላችሁ የመቱ ዩኒቨርሲቲ መምህራን በሙሉ

የድህረ ምረቃ ትምህርት እየተማራችሁ ላላችሁ የመቱ ዩኒቨርሲቲ መምህራን በሙሉ በመጀመሪያ የከበረ ሠላምታችንን እናቀርባለን፡፡
በመቀጠል ለድህረ ምረቃ ትምህርት ውል ከዚህ በኋላ ውል ሰጭ እየተባለ የሚጠራው መቱ ዩኒቨርሲቲና ውል ተቀባይ እየተባለ የሚጠራው /ትጠራው የዩኒቨርሲቲያችን መምህራን መካከል የተደረገውን ውል ግምት ውስጥ በማስገባት በውሉ አንቀጽ “7” እና ውሉ ላይ ተሻሽለው የገቡትን ሃሳቦች በጥሞና በመረዳት ከዩኒቨርሲቲያችሁ ጋር እየተነጋገራችሁ ትምህርታችሁን በላቀ አፈጻፀም እንድትከታተሉ እያሳሰብን የውሉን አንቀጽ “7” እና ተጨማሪ ሀሳቦችን እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

አንቀፅ 7
ውል ተቀባይ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ገጥሞት/ሟት/ ትምህርቱን/ቷን/ ለማቋረጥ ወይም የስልጠና ጊዜውን ለማራዘም ሲገደድ /ስትገደድ/ ለውል ሰጭው ያገጠመውን /ማትን/ ችግር በበቂ ማስረጃ አስደግፎ ችግሩ ባጋጠመው/ማት/ በ10 ቀናት ውስጥ በፅሁፍ የማሳወቅ ግዴታ ሲኖርበት/ባት/ ከተወሰነው ጊዜ ውጭ የሚቀርብ ጥያቄና ማስረጃ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ውል ሰጭም በተወሰነው ጊዜ ውስጥ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን መርምሮ ተገቢውን ውሳኔ የመስጠት ኃላፊነት ይኖርበታል።
ይሁን እንጂ አብዛኛዎቹ መምህራኖቻችን በፈረሙት ውል አግባብ ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ስራቸው እየተመለሱ በማስተማር የዜግነት ግዴታቸውን እየተወጡ ያሉ ቢሆንም ጥቂት መምህራኖች ግን በፈረሙት ልክ ህጉን እየተገበሩ አይገኙም ፡፡
በመሆኑም በዩኒቨርሲቲያችን እስፖንሰርነት የMSc/ PhD ትምህርታችሁን እየተማራችሁ ያላችሁ መምህራን በሙሉ፤
1. በየሴሚስቴሩ የተመዘገቡበትን /registration Slip/ ለዩኒቨርሲቲው ሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት እና ለፋካልቲያቸው መላክ አለባቸው፤
2. ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ትምህርታቸው የሚራዘም ከሆነ ከሚማሩበት የድህረ- ምረቃ ት/ቤት ትምህርቱ የተራዘመበትን የሚገልጽ ደብዳቤ ለዩኒቨርሲቲው ሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት እና ለፋካልቲያቸው ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል ፤
3. የPhD ተማሪዎች የደረሳችሁበትን /progress report/ ለዩኒቨርሲቲው ሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት እና ለፋካልቲያቸው ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ዋሶቻቸው ለትምህርት ሲሄዱ /በዝውውር ዩኒቨርሲቲውን ሲለቁ ሌላ ዋስ የመተካት ግዴታ አለባቸው ፡፡
5. የግላቸውንና የሚማሩበትን ዩኒቨርሲቲ websit, e-mail, p.o.box ከተቻለ ከመሄዳቸው በፊት ካልሆነ ግን ት/ት ከመጀመራቸው በፊት ለዩኒቨርሲቲያችን ሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት እና ለፋካልቲያቸው መላክ ይጠበቅባቸዋል፡፡
6. ከተ/ቁ1-5 እና በአንቀጽ “7” የተዘረዘሩት የውል ተቀባይ ግዴታዎች ካልተሟሉ ዩኒቨርሲቲው ውሉን ለማቋረጥ ስለሚገደድ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲደረግ እያሳሰብን የተጣለብንን የሕዝብና የሀገር ኃላፊነት ከግንዛቤ በማስገባት ለትምህርታችሁ ትኩረት ሰጥታችሁ እንድትማሩ እያበረታታን መልካሙን ሁሉ እንመኛለን፡፡
ከሠላምታ ጋር
መቱ ዩኒቨርሲቲ የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት

News_Image: