ማስታወቂያ

ለመቱ ዩኒቨርሲቲ ነባርና አዲስ የተመደባችዉ ተማሪዎች በሙሉ
የመቱ ዩኒቨርሲቲ ነባርና አዲስ መደበኛ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የምዝገባ
1. ለነባር የቅድም ምረቃ ተማሪዎች ከመስከረም 21- 22/2012 ዓ.ም በቅጣት መሰከረም 23-24/2012 ዓ.ም ሲሆን
2. ለአዲስ ቅድመ ምረቃ ተማሪዎች መስከረም 28-30/2012ዓ. ም በቅጣት: ጥቅምት 1-3/2012 ዓ.ም
አዲስ ገቢ ቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ስትመጡ
1. የ8ኛ፣ 10ኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ያጠናቀቃችሁበት ውጤት ዋናውና ፎቶ ኮፒ፣
2. ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ፎቶ ኮፒ፣
3. አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ
4. ስምንት 3*4 ጉርድ ፎቶ ግራፍ ይዛችሁ እንድትመጡእናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ ለሁሉም የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች
1. ከምትኖሩበት ወረዳ ውል የያዛችሁበት ቅጽ ህጋዊ ማሀተም ያለበት ይዛችሁ መምጣት ይጠበቅባችዋል፡፡
2. የ2011 ዓ.ም የአንደኛ ዓመት የነበራችሁና ለሁለቱም ሴሚስተሮች በህጋዊ መልኩ “With draw” ሞልታችሁ ወይም በ”Academic dismissal for Readmission” ሆናችሁ የወጣችሁ ተማሪዎች ከአዲስ ገቢ ተማሪዎች ጋር ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡
3. ከላይ በተጠቀሰው ቀናት በፊትም ሆነ ዘግይቶ የሚመጡትን ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
4. በበደሌ ግብርናና ደን ሳይንስ ኮሌጅ የተመደባችአዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ በበደሌ ካምፓስ ብቻ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የመቱ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስተራር ዳይሬክቶሬት