የምዝገባ ጥሪ ለውጥ ማስታወቂያ

በ2009 ዓ/ም በመቱ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ
ቀደም ሲል በ2009 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በመቱ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው ጥቅምት 14-15/2009 ዓ/ም
በቅጣት ምዝገባ ጥቅምት 16-17/2009 ዓ/ም መሆኑን መግለፃችን ይታወሳል፡፡
ሆኖም ግን ከላይ የተገለጸው የምዝገባ ቀናት ወደ ጥቅምት 24-25/2009 በቅጣት ጥቅምት 26-27/2009 የተቀየረ መሆኑን እያሳወቅን
ለምዝገባ ስትመጡ
1. 3x4 የሆነ 8 ጉርድ ፎቶግራፍ
2. የ8ኛ፣ 10ኛ ና 12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ
3. ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስና የስፖርት ልብስ ይዛችሁ እንድትመጡ
ከተባለው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

Pages