አስደሳች ዜና ለከፍተኛ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

መቱ ዩኒቨርሲቲ በ2009 ዓ/ም በመደበኛና በእረፍት ቀናት የትምህርት ፕሮግራም በማስተርስ መርሃ ግብር ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የትምህርት መስኮች አዲስ አመልካቾችን ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በሚፈለጉት የትምህርት ዓይነቶች በመመዝገብ የዕድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል፡፡
በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋካልቲ በማስተርስ ዲግሪ በሁለት ፕሮግራሞች ማለትም
• በማስተርስ ኦፍ ቢዝነስ አድሚስትሬሽን (MBA)
• በማስተርስ ኦፍ አካውንቲንግ ኤንደ ፋይናንስ (MSC)
በማህበረሰብ ጤናና ሜዲካል ሳይንስ ፋካልቲ በማስተርስ ዲግሪ በአንድ ፕሮግራም ማለትም
• ማስተርስ ኦፍ ፐብሊክ ሄልዝ (MPH)
አመልካቾች ቢያንስ ሁለት ዓመት የስራ ልምድ ያላቸውና ሙሉ የትምህርት መረጃ ኦሪጅናልና ሪኮሜንዴሽን ሌተር በሦስት ኮፒ እንዲሁም ሦስት ጉርድ ፎቶግራፍና ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

Pages

Latest News

የመቱ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በደቡብ ሱዳን ሙርሌ ጎሳ ታጣቅዎች ለተገደሉት ንጹሓን ዜጎች የተሰማውን ሀዘን ገለፁ

የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ይህን ሀዘናቸውን የገለጹት በሻማ ማብራት ስነ ስርዓት ሲሆን በዚህ ወቅትተሳታፊዎቹ በሰጡት አስታያየት ድርግቱ በንጸሐን ዜጎች ላይ መፈፀሙ ያሳዘናቸው መሆኑን ገልታ መንግስትም ይህ ኢሰብአው ድርግት በፈጸሙት ላይ አስገላጊውን እርምጃ በመውሰድ በታጣቅዎቹ ታፍነው ተወሰዱት ሕጻናትና ሴቶች የማዳን ስራ በአፋጣኝ እንዲወስድ ብለዋል፡፡ በተጨማሮም መንግስት ንጹሐን ዜጎች ለማዳንና ለተጎጂ ቤተሰብ በሚያደርገው ድጋፍ ከመንግስት ጎን መሆናቸውን ገልጸው ለተጎጂ ቤተሰቦች፣ ለጋምቤላ ክልል ህዝብና መንግስት መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡ በዚህ የሳማ ማብራት ስነስርዓት ላይ

Read more
የመቱ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ለሁለተና ጊዜ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚሆን ቦንድ ለመገዛት ቃል ገቡ

5ኛ ኣመት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል ለሀለተኛ ጊዜ ቦንድ ለመግዛት ቃል ገቡ፡፡ በዚሁ የቦንድ ግዥ ፕሮግራም ላይ የግድቡን የእስካሁን ሂደት የመወያያ ጽሑፍ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበ ት በኃላ ነው ይህ ቃል የተገባው፡፡ ይህ የቦንድ ግዥ ቃል የተገባው በዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞችና ተማሪዎች ናቸው፡፡

Read more
የመቱ ዩኒቨርሲቲ ከኢሉ አባቦር ግብርና ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የግብርና ቴክኖሎጂ ሽግግርና የማሀበረሰብ ንቅናቄ ስልጠና መድረክ አካሄደ

የመቱ ዩኒቨርሲቲ ከኢሉ አባቦር ግብርና ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የግብርና ቴክኖሎጂ ሽግግርና የማሀበረሰብ ንቅናቄ ስልጠና መድረክ አካሄደ፡፡ የንቅናቄ መድረክ ስልጠናው የተካሄደው የመቱ ዪኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎትና ማማከር ዳይሬክቶሬት ከኢሉ አባቦር ዞን ግብርና ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ነው፡፡ በዚሁ የንቅናቄ መድረክ ላይ በዩኒቨርሲቲው ምሁራንና በዞኑ የግብርና ባለሙያዎች የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቃምና የተገኙ ውጤቶች አስመልክቶ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በመድረኩ ላይ የተገኙት ባለድርሻ አካላትም በጥናት ጽሑፎቹ ላይ የዞኑን ነባራዊ ሁኔታ የሚያሳይ መሆ

Read more
የመቱ ዩኒቨርሲቲና የአካባቢው ማህበረሰብ በግንባታ ላይ ያለውን የያዮ ማዳበሪያ ፋብሪካ ጎበኙ

የመቱ ዩኒቨርሲቲና የአካባቢው ማህበረሰብ በግንባታ ላይ ያለውን የያዮ ማዳበሪያ ፋብሪካን ጎበኙ፡፡ የጉብኝቱም ኣላማም የፋብሪካው ግንባታ ሂደት ምን እንደሚመስልና ለወደፊቱ ለአካባቢው ና ለዩኒቨርሲቲው ያለውን ጠቀሜታ ለመረዳት እንደሆነ ተገልጧል፡፡ በጉብኝቱ ወቅትም የፋብሪካው የስራ ኃላፊዎች ስለግንባታውና የወደፊት ስራ ገለጻ ሰጥተዋል፡፡ በተጨማሪም ፋብሪካው በዋናነት እንደግብዓት የሚጠቀምበት የከሰል ድንጋይ ማውጫ ጉብኝት ተደርጓል፡፡ ፋብሪካው በውስጡ ያካተታቸው ከከሰል ድንጋይ የሚመነጭ 90 ሜጋዋት ኃይል ማመንጫ፣ የፎስፌት ፋብሪካና የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካዎች መሆኑ ተገ

Read more
Ethics and Anti Corruption Activities on Progress

MeU Ethics and Anti Corruption directorate has the vision of producing citizens who will fight corruption by developing and internalizing the concept of good governance.

Read more

Pages