የህዝብና ውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ግንቦት 11/2014 ዓ. ም
መቱ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ ካፍ፣ ኦሮሚያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና ከኢሉ አባቦር ዞን ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለአስራ አንድ ቀናት ስሰጥ የነበረው የአሰላጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ ስልጠናው የተሰጠው የሀገሪቱን እግር ኳስ በተተኪው ትውልድ ሁሉን ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ያለውን ስራ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ነው፡፡ ይህ ስልጠናም የካፍ የዲ ደረጃ ያለው የአሰልጣኝነት ስልጠና ነው፡፡ ይህ ስልጠና በአካባቢው የእግር ኳስ ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊዎች ደረጃውን የጠበቀ ስልጠና አግኝቶ ተተኪ ስፖርተኞች እንድሆን የሚረዳ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡ ሰልጣኖችም በስልጠና ው ማብቂያ ላይ ባነሱት ሃሳብ የእግር ኳስ የአሰልጣኝነት ስልጠናው በንድፈ ሃሳብና በተግባር ስሰጥ የቆየ ሲሆን ሰልጣኞቹም ከስልጠና ብዙ ዕውቀትና ልምድ እንደቀሰሙበት ተናግረዋል፡፡ በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የመቱ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ለታ ዴሬሳ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲያችን ለስፖርቱ ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነና ለሰልጣኞችም ይህ ስልጠና ለእግር ኳስ ዘርፉ እድገት የቃል ኪዳን ሰነድ መሆኑን፣ እንዲሁም በአካባቢው የቀዘቀዘውን የእግር ኳስ እንቅስቃሴ ያነቃቃል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው ለአጠቃላይ የስፖርት ዘርፉ የጀመረውን ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መጥተው ስልጠናውን የሰጡ እንስትራክተሮች እንድገለጹትም ሰልጠኞቹ ለስልጠናው የነበራቸው ተነሳሽነትና ሞራል እንድሚያደንቁ ገልጸው ለወደፊት ይህንን የእግር ኳስ ዘርፍ ለማሳደግ በቤተሰባዊነት ስሜት አብሮ እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡
በዚህ ስልጠና ላይ መቱ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ ከሁሉም የዞኑ ወረዳዎች ከሚገኙ የእግር ኳስ ባለሙያዎችና ከዚህ በፊት በተለያዩ ክለቦች ሲጫወቱ የቆዩ 29 ሰልጣኞች ናቸው፡፡ በመጨረሻም ሰልጣኞቹ የአሰልጣኝነት የምስክር ወረቀት ከዕለቱ የክብር እንግዳ ከዶ/ር ለታ ዴሬሳ፤ እንዲሁም ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ እንስትራክተሮችና ከኢሉ አባቦር ዞን ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ተወካይ እጅ ተቀብላዋል፡፡

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.