መቱ ኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ሲያስተምራቸው የነበረ ተማሪዎችን ለ7ኛ ዙር በደማቅ ስነስርዓት አስማረቀ፡፡ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎቹን ያስመረቀው በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር በመጀምሪያ ዲግር 2789 ሲሆን በሁለተኛ ዲግሪ 107 ተማሪዎች ነው፡፡

በዚህ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የዕለቱ የክብር እንግዳ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስተር የሆኑት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለተመራቂ ተማሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት ያለፉት ተደራራቢ ፈተና አልፋችሁ እንኳን ለስኬት በቃችሁ ብለዋል፡፡ የዓመቱ የምረቃ በዓል የፈተናም፣ የስጋትም፣ በመጨረሻም የስኬት ማሳያ ስለሆነ ለሕይወታችሁም በሕይወታችሁም ብዙ የተማራችሁበት እንደሆነ አምናለው፡፡ በባለፉት ጥቂት ዓመታት እንደሀገር የጀመርናቸው የለውጥ ስራዎች እንዳይሳኩ ጥቅማችንና ህልውናችን ላይ የተጋረጡ ፈተናዎች በመስዋዕትነትና በብልሃት ለመቀልበስ ተችሏል፡፡ በተመሳሳይ ትምህርት ተቋሞቻችንና ማህበረሰቡ ከዋና ዋና የሀገርና የትውልድ ከማዳን ስራ ተወጥተው በሌላ አጀንዳ ሀብቱንና ጊዜውን ስያጠፋ፤ ፈተና ሲያጋርጡ የነበሩ አካላት ፈተና ተቋቁመን ዛሬ ተመራቂዎቻችን ማስመረቅ መቻላችን እንደ ትልቅ ስኬትና እንደ አንጸባራቂ ድል እንቆጥራለን ካሉ በኋላ ዩኒቨርሲቲው ችግር ሲያገጋጥም ከጎኑ በመቆም ችግሮችስትፈቱ የነበራችሁ አካላት ሁሉ በሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ስም የላቀ ምስጋና ማቅረብ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡ ዶ/ር እንደገና አበበ የመቱ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ባደረጉት ንግግር ዩኒቨርሲቲያችን እንደሀገር ባጋጠመው አለመረጋጋትና የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተገዳሮት አልፋችሁ ለዚህ መብቃታችሁ የሚያኮራ ነው ካሉ በኋላ ተመራቂ ተማሪዎች በቀሰሙት ዕውቀትና ክህሎት ህዝባቸውንና ሀገራቸውን በታማኝነት እንዲያገሉግሉ አደራ የተጣለባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚህ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ለቅድሞዎቹ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንቶች ዶ/ር መኮንን ዲንኮና ለዶ/ር ታደሰ ሀብታሙ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው በአካባቢው እንድከፈት ከጅምሩ ጥያቄ ሲያቀርቡ የነበሩና ለእስካሁን ስኬቱ ከዩኒቨርሲቲው ጎን ለነበሩት ለአቶ አረጋ ጌላና ለወ/ሮ ኑሪያ ከድር ዕውቅና ሰጥተዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎቹን ያስመረቀው በመቱ ዋናው ካምፓስና በበደሌ ግብርናና ደን ሳይንስ ኮሌጅ ነው፡፡ መቱ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ወቅት በሰባት ኮሌጆችና በአንድ ትምህርት ቤት በመጀመሪያ ዲግሪ አርባ ስድስት ትምህርት ክፍሎችና በአስራ ስምንት ፕሮግራሞች ትምህርት እየሰጠ ይገኛል፡፡

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.