ዩኒቨርሲቲው ያስመረቃቸው በማህበረሰብ ጤናና ሜድካል ሳይንስ ኮሌጅ ስር በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ስማሩ የቆዩት የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ናቸው፡፡ ዩኒቨርሲቲው ካስመረቃቸው ተማሪዎች የፋርማሲ ትምህርት ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረቁ ናቸው፡፡ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የመቱ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ደዶ/ር እንደገና አበበ እንደገለጹት ተመራቂ ተማሪዎችን እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ የተጣለባችሁን አደራ በትጋትና በታማኝነት እንድትወጡ ብለዋል፡፡ በተጨማሪም መቱ ዩኒቨርሲቲ ተደራሽነቱ በማስፋት በጎሬ ከተማ የመማሪያ ሪፈራል ሆስፒታል ለማስገንባት የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አጠናቆ ወደ ግንባታ እየገባ ነው ብለዋል፡፡ በዕለቱ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይበክብር እንግድነት የተገኙት የኢሉ አባቦር ዞን ዋና አስተዳደርና የመቱ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታሪኩ ነጋሽ ባስተላለፉት መልዕክት ባገኛችሁት ዕውቀት ለህዝባችሁንና ለሀገራችን ኢትዮጵያ ሁለናተናዊ ብልፅግና የድርሻቸውን እንደወጡ ከአደራ ጭምር አሳስበዋል ብለዋል፡፡

በዕለቱም ዩኒቨርሲተው 336 ተማሪዎችን በያስመረቀ ሲሆን ከነዚህም ተማረቂዎች 19 ተማሪዎች የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ናቸው፡፡

በዚህ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ላለፉት በርካታ ዓመታት የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ለመፍታት በግብርና፣ በትምህርትና በጤና ተቋማት ማስፋፋት እፍል ስራዎችን የሰሩት የሰዎች ለሰዎች ዕርዳታ ድርጅት አመራር ለሆኑት ለወ/ሮ አልማዝ ቦም ዕውቅና ሰጥተዋል፡፡

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.