በተጨግንዛቤ መስጨበጫ ስልጠናው ለሁለት ቀናት የተሰጠ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ እና አስተዳደር ዘርፍ መካከለኛ አመራሮች ተሳትፎበታል። በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በተዘጋጀው ሀገራዊ የከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲ እና እቅዶች ላይ ሰፊ ማብራርያ የተሰጠ ሲሆን: በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ላይም:-

🍍 የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የአሥር ዓመት ልማት ዕቅድ በሚል ርዕስ በቀረበው ማብራርያ የከፍተኛ ትምህርት ጥራት፤ ተደራሽነት፤ ፍትሐዊነት እና አግባብነትን ለማረጋገጥ የምያስችሉ የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች ቀጣይ ትኩረቶች እና የሚጠበቁ ውጤቶች በዝርዝረ ተብራርቷል፡፡
🍍ብሔራዊ የሳይንስ ፖሊሲና ስትራቴጂ፡ የኢትዮጵያን ብልጽግና በሳይንሳዊ ዕውቀት ለመምራት አገር በቀል ዕውቀቶችን እና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በእውቀት ላይ የተመሠረተ ልማት ማስፋፋት እንድቻል አስተዳደርና አመራሩ፤ የኢንተርፕራይዝ ልማት፤ ሳይንሳዊ ምርምርና ፈጠራ እንድሁም ፋይናንስና የማበረታቻ ስርዓትን በመዘርጋት ጠንካር ሀገራዊ፤ አህጉራዊና ዓለማቀፋዊ ትብብርና አጋርነትን መገንባት የሚሉ ነጥቦች ተነስቷ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት ወይይት ተደርጎበታል።
🍍ከዚህም በተጨማሪ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የቅበላ እና ምደባ ፖሊሲ፡ ሐገራዊ ኢኮኖሚን የተቋማት የመቀበል አቅምንና የትኩረት መስክ ልየታን መሰረት ያደረገ በተማሪዎች ብቃት ፍላጎትና ዝንባሌ ላይ የተመሰረተ የትምህርት ጥራት መርህን ያገናዘበ ግልጽ ፍትሐዊና የዉድድርን መርሕን የተከተለ እንዲሆን ልዩ ድጋፍን ያካተተ የተማሪዎች ቅበላ እና ምደባ ስርዓት ለመዘርጋት የተዘጋጀ ፖሊሲ መሆኑን በማነሳት ውይይት ተደርጎበታል፡
የተሰጠውን ማብራርያ እና በፅሁፍ የቀረበላቸውን ዶክመንት መነሻ በማድረግ የስልጠናው ተሳታፊዎች በጥልቀት ወይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱም ለቀረቡት ጥያቄዎች በአቅራቢ አመራሮች ማብራሪያ የተሰጠበት ሲሆን ቀሪ ሀሳቦች እና ጥያቄዎች ደግሞ ሀገራዊ የትምህርት ፖሊሲውና ስትራቴጅክ ዕቅዱ ተግባራዊ በምደረግበት ወቅት ለግብዓትነት እንደምያገለግሉ በመግባባት የግንዛቤ መስጨበጫ ስልጠናው ተጠናቋል፡፡
ማሪ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የቅበላ እና ምደባ ፖሊሲ፡ ሐገራዊ ኢኮኖሚን የተቋማት የመቀበል አቅምንና የትኩረት መስክ ልየታን መሰረት ያደረገ በተማሪዎች ብቃት ፍላጎትና ዝንባሌ ላይ የተመሰረተ የትምህርት ጥራት መርህን ያገናዘበ ግልጽ ፍትሐዊና የዉድድርን መርሕን የተከተለ እንዲሆን ልዩ ድጋፍን ያካተተ የተማሪዎች ቅበላ እና ምደባ ስርዓት
የተሰጠበት ሲሆን ቀሪ ሀሳቦች እና ጥያቄዎች ደግሞ ሀገራዊ የትምህርት ፖሊሲውና ስትራቴጅክ ዕቅዱ ተግባራዊ በምደረግበት ወቅት ለግብዓትነት እንደምያገለግሉ በመግባባት የግንዛቤ መስጨበጫ ስልጠናው ተጠናቋል፡፡

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.