በመቱ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና ተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዚደንት ጽ/ቤት የቡኖ በደሌ እና ኢሉ አባ ቦር ዞኖች የዉሃ ልማትና የመብራት ኃል ቢሮዎች ጋር ምክክር አደረጉ።

በመቱ ዩኒቨርሲቲ የዉሃና የኤሌክትሪክ አገልግሎት አቅርቦትን ለማሻሻልና ቀልጣፋ ለማድረግ ታሥቦ ከባለድርሻ አካላት ጋራ ለመወያየት በበደሌ ከተማ የተዘጋጀዉን የዉይይት መድረክ በንግግር የከፈቱት የመቱ ዩኒቨርሲት አስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕ/ት ዶ/ር ተካልኝ ቀጄላ ሲሆኑ፡ የዉሃና የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለዩኒቨርሲቲ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆኑ ለዩኒቨርሲቲዎች የመኖር ያለመኖር ጉዳይ ስለሆነ ከነዝህ አገልግሎት ሰጪ ቢሮዎች ጋር መወያየትና አገልግሎቱን ማሣለጥ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።

የ2012 የዘርፎቹ አገልግሎት አሰጣጥን የሚዳስስ ጽሁፍ እየቀረበ ስሆን በሚቀርበዉ ጽሑፍ ላይ ዉይይት ተደርጎ የነበሩ ክፍተቶች ተለይተዉ ለወደፊት በቅንጅት የሚሠራበትን አሰራር እንደሚዘረጋ ከወጣዉ መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል።

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.