መቱ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
27/9/2013 ዓ.ም
መቱ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ ከኢሉ አባበር ዞን ወረዳዎች ለተወጣጡ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ፈጠራ ስልጠና ተሰጠ፡፡
የስራ ፈጠራ ስልጠናው የተሰጠው የተለያዩ ከኢሉ አባበር ዞን ወረዳዎች ለተወጣጡ ስራ አጥ ለሆኑ ወጣቶች ነው፡፡ ሰልጣኝ ወጣቶች ከስልጠናው ባገኙት ክህሎት የራሳቸው ስራ ፈጥረው መስራት ይችላሉ፡፡ ሰልጣኝ ወጣቶች የተሰጣቸው ስልጠና ያለባቸውን የስራ አጥነት ችግር እንደሚፈታ ገልጸው፣ ወጣቶቹ የክዕሎት ስልጠና አግኘተው ስራ ፈላጊ ሳይሆኑ ስራ ፈጣሪ ሆነው በአከባቢያቸው በሚያገኙት የገበያ ፍላጎት ላይ መሰረት አድርገው የስራ ዕድል ፈጥረው እራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን መርዳት የሚችሉበት እውቀት እንዳገኙ ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይም የደረቅና ፈሳሽ ሳሙና አመራርት ላይ በዘርፉ ለተደራጁ ወጣቶች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ በስልጠናውም የደረቅና ፈሳሽ ሳሙና አመራረትና በገበያ ውስጥ እንዴት ዘልቀው መግባት በሚችሉበት ላይ ነው የተሰጣቸው፡፡
ስልጠናው ስልጠናው የሚሰጠው በዩኒቨርሲቲው በቂ ዕውቀትና ክህሎት ባላቸው መምህራን መሆኑን ጠቅሰው ስልጠናው በተግባር የተደገፈ ጭምር እንደሆነ መ/ር ስማገኘው መላኩ ማማከርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ገልፀዋል፡፡
ይህ ስልጠና የተሰጠው ከግንቦት 23/2013 ዓ. ም ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት ነው፡፡

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.