ነሐሴ 24/2013 ዓ.ም
መቱ ዩኒቨርሲቲ ከ2800 በላይ ተማሪዎችን ለ8ኛ ዙር ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተገለፀ ፡፡

መቱ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን ከ2800 በላይ ተማሪዎችን ለ8 ኛ ዙር ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተገለፀ ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በ2004 ዓ.ም 300 ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር ማስተማሩን ስራ የጀመረ ሲሆን በ2006 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ 131 ተማሪዎችን አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማሩን ስራ አጠናክሮ በመቀጠል እንዲሁም የሚሰጣቸውን የትምህርት መስኮች በማስፋፋት ከአስር ሺህ በላይ ሰልጣኞችን በተለያዩ የሙያ መስኮች አሰልጥኖ ማስመረቅ እንደቻለ ታውቋል፡፡ በዘንድሮው የትምህርት ዘመንም ዩኒቨርሲቲው በ2012 ዓ.ም በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት ተስተጓጉሎ የነበረውን ትምህርት በማስቀጠል በመጀመሪያ ዲግሪ ከ2500 በላይ እንዲሁም በሁለተኛ ዲግሪ ከ250 በላይ ተማሪዎችን በመደበኛና በተከታታይ ትምህርት መርሃ ግብር ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት መ/ር ገረማ አለማየሁ ገልፀዋል፡፡

በተጫመሪም ዩኒቨርሲቲው በሰባት ኮሌጆችና በሶስት ትምህርት ቤቶች 47 የመጀመሪያ ድግሪ እና 28 የሁለተኛ ዲግሪ የትመህርት ፕሮግራሞች ስልጠና እየሰጠ ያለ ሲሆን በዘንድሮው የትምህርት ዘመንም በእነዚህ የተለያዩ የትምህርት መስኮች ከ2800 በላይ በሙያ እና በስነ ምግባር የታነፁ ሙያተኞችን ለ8ኛ ዙር በደማቅ ሁኔታ ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ መሆናቸው ተጠቁመዋል፡፡

ህዝብና ውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.