መቱ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢውን የወተትና የስጋ ምርት ማሻሻል የሚያስችል የዳልጋ ከብት ማሻሻያ ፕሮጀክት የማዳቀል መርሃ ግብር በይፋ አስጀመረ፡፡

ፕሮጀክቱ የተጀመረው በመቱ ዩኒቨርሲቲ የበደሌ ካምፓስ ነው፡፡ ይህንን ፕሮጀክት ያስጀመሩት በመቱ ዩኒቨርሲቲ የበደሌ ካምፓስ ዲንና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ኦዳ ግዛው በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክትም ፕሮጀክቱ በአካባቢው የሚገኙ ከብቶች የወተትና የስጋ ምርት ለማሻሻል ታስቦ የተጀመረ ሲሆን ይህም በቴክኖሎጂ የታገዘ የማዳቀል ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡ በዚሁ መሰረቱ ፕሮጀክቱ በቡኖ በደሌ ዞን በደሌ ወረዳ የተጀመረ ሲሆን በቀጣይም በኢሉ አባቦር ዞን በመቱ ወረዳ በተመረጡ ቀበሌዎች ላይ እምደሚጀመር ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም በዚህ ዓመት ከሁለቱም ዞኖች ሁለት ሺህ የሚሆኑ የአርሶ አደሩ ላም ሳይንሳዊ በሆነ መንግድ እንደሚዳቀሉ ገልፀው ስራው በቀጣይ ዓመት በስፋት ይሰራበታል ብለዋል፡፡

ይህንን ፕሮጀክት ለማስጀመር በጥናት የተደገፈ ስራ ስሰራ መቆየቱን ጠቅሰው ለስራው ስኬታማነት ለባለሙያዎች አስፈላገው ስልጠና መሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ አርሶ አደሮች በሰጡት አስተያየትም ይህንን ዕድል በማግኘታቸው መደሰታቸውን ገልፀው በቀጣይ የመቱ ዩኒቨርሲቲ ተመሳሳይ ስራዎችን ለህብረተሰቡ መስራት አለበት ብለዋል፡፡

ይህ ፕሮጀክት ከሁለት ዓመት በፊት የእኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ኦሮሚያ ከሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ማለትም በመቱ ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪነት ከወለጋ፣ ጂማና አምቦ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.