መቱ ዩኒቨርሲቲ የ2013 ዓ.ም የሥራ ዘመን የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ለዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ አቀረበ።
ዛሬ ጥቅምት 21/2013 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲዉ እቅድ፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት የ2013 ዓ.ም ስራ ዘመን የአንደኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ለመላ የዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሠብ አቅርቧል።
በዝሁ መድረክ የ2012ዓ.ም የዉስጥ የት/ት ጥራት ኦዲት ዉጤት ሪፖርት በዩኒቨርሲቲዉ የት/ት ጥራትና አግባብነት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የቀረበ ሲሆን በቀረቡት ሁለቱም ሪፖርቶች ላይ ዉይይት ከተካሄደ በኋላ ከ2012 ዓ.ም እና ከዝያ በፊት የእርፍት ጊዜያቸዉን በመሠዋት ዩኒቨርሲቲዉን ሲያገለግሉ ለቆዩ የሥራ ክፍሎች እና በዉስጥ የጥራት ኦዲት የተሻለ ዉጤት ላሥመዘገቡ ፋኩልቲዎችና የት/ት ክፍሎች የምሥክር ወረቀት ተሠጧል።
የዩኒቨርሲቲዉ የበላይ አመራሮች በሠድረኩ ላይ የተገኙ ስሆን ዩኒቨርሲቲዉ አሁን ያለበትን ደረጃ የደረሰዉ በሁሉም የተቋሙ ሠራተኞች ጥረት ድምር መሆኑን ገልፀዉ ለወደፊትም በትብብርና በአንድነት መንፈስ ከቸሠራ የበለጠ ዉጤት ማምጣት እንደሚቻል አስገንዝበዋል።
በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝደንት ዶ/ር እንደገና አበበ የወደፊት ትኩረትና የስራ አቅጣጫ በመሥጠት መድረኩን ቋጭተዋል።