መስከረም 26/2014 ዓ. ም
የህዝብና ውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
መቱ ዩኒቨርሲቲ 330 ለሚሆኑ የኢኮኖሚ ችግር ላለባቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡ ድጋፉ የተደረገው በኢሉ አባቦር ዞን ያዮ ወረዳ ያዮ ከተማና በበቾ ወረዳ ለሚገኙና የኢኮኖሚ ችግር ላለባቸው ተማሪዎች ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው ድጋፉን ያደረገው ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ካሰባሰበው የገንዘብ ድጋፍና በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አገልግሎት በኩል ነው፡፡ ድጋፉን በስፍራው ተገኝተው የሰጡት የመቱ ዩኒቨርሲቲ የምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎትና ትብብር ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር በድሉ ተካ ሲሆኑ በዚህ የድጋፍ ስነስርዓት ላይ እንደተናገሩት የዛሬው ተማሪዎችና ድጋፍ የሚትሹ ነጌ ተምራችሁ ራሳችሁን እንድትችሉ ታስቦ የተደረገ ሲሆን ዛሬ በተደረገላችሁ ድጋፍ በመነሳሳት በትምህርታችሁ እንድትበረቱ እመክራችኋለሁ ብለዋል፡፡ በቀጣይም ይህንን የድጋፍ ስራ ተጠናክረው የሚቀጥል መሆኑን ተናግዋል፡፡ ድጋፉን ማህበረሰቡን በማስተባበር ካሰባሰቡት አንዱ የሆኑት ዶ/ር ጋሩማ አብዲሳ እንደተናጉት ዛሬ የተደረገው ድጋፍ ከዩኒቨርሲቲውና ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ነው፡፡ ስለዚህ ድጋፉ ታሳቢ ያደረገው ትምህርታችሁን እንዳታቋርጡና ነጌ ተምራችሁ ማህበረሰቡ ያደረገላችሁን ድጋፍ በዕጥፍ እንድትመልሱ ነው ብለዋል፡፡
የያዮ ከተማ አስተዳደር በመወከል ድጋፉን ተረክበው ለተማሪዎች የሰጡት አቶ ዮሐንስ ምትኩ
እንደተናጉት ዛሬ መቱ ዩኒቨርሲቲ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን ገልፀው ዩኒቨርሲቲው በዞኑ እያደረገ ያለው የማህበረሰብ አገልግሎት ለሌሎች ተቋማት አርኣያ የሚሆን ነው፡፡ ስለዚህ ዩኒቨርሲቲው ለወደፊት በሌሎች ስራዎችም ከወረዳው ጋር እንደምሰራ ዕምነታቸውን ገልፀዋል፡፡
በተመሳሳይ የበቾ ወረዳ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ካሰች አያና እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ተማሪዎችም በትምህርታቸው በርትተው ውጤት እንዲያስመዘግቡ አደራ ብለዋል፡፡

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.