መስከረም 19/2014 ዓ.ም
መቱ ዩኒቨርስቲ ከCAMARA EDUCATION ጋር በመተባበር ስልጠና መስጠት ጀመረ።

መቱ ዩኒቨርስቲ ከCAMARA EDUCATION ጋር በመተባበር በኢሉ አባ ቦር ዞን እና በቡኖ በደሌ ዞን ወረዳዎች ውስጥ ለሚገኙ 16 የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ርዕሳነ መምህራን፣ ሱፐርቯይዘሮች፣ መምህራን እና የICT ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ጀመረ።

በዛሬው ዕለት የተጀመረው ስልጠና ለተከታታይ ስድስት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን ትኩረቱም ዩኒቨርሲቲው ከCAMARA EDUCATION ጋር በመተባበር ለትምህርት አገልግሎት ብቻ የሚውሉ ከ45 ሺ በላይ የሁሉም የትምህርት ዓይነት ዋቢ መጽሐፍ የተጫኑባቸው የዴስክ ቶፕ ኮምፒዩተሮች ድጋፍ ለትምህርት ቤቶች ለመስጠት እንዲያመች ለትምህርት ቤቶቹ ባለ ድርሻ አካላት ግንዛቤ ለመስጠት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

በስልጠናው መከፈቻ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርስቲው የምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎት እና ትብብር ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር በድሉ ተካ እንደተናገሩት ፤ ለአንድ ሀገር እድገት የተማረ የሰው ሀይል ወሳኝ በመሆኑ ይህንን የሰው ሃይል ለሟሟላት የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ እና ትምህርትን በሳይንስና ቴክኖሎጂ መደገፍ ወሳኝ ነው ብሏል። ዶ/ር በድሉ አያይዘውም ዩኒቨርሲቲው በአካባቢው የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላይ (STEM) ማዕከላትን ማደረጀት የተጀመረውን ስራ በሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ላይ ለማድረስ አጠናክሮ እንደሚሰራ የገለፁ ሲሆን አሁን በዚህ ዙር ከCAMARA EDUCATION ጋር በትብብር የተገኘውን የኮፕዩተር ድጋፍ ያገኙ ት/ቤቶችም ኮምፒዩተሮቹን ለተገቢው ዓላማ በማዋል ለቀጣዩ ትውልድ አገልገሎት መስጠት እንዲችል በተገቢው ጥንቃቄ መያዝ እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፏል።

መቱ ዩኒቨርስቲ በዚህ ዙር ከሁለቱ ዞኖች ለተወጣጡ ለ16 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከCAMARA EDUCATION ጋር በመተባበር 400 ኮምፒውተሮችን ለማከፋፈል ዝግጅት እንዳጠናቀቀ የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አገልግሎት እና ማማከር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መ/ር እሸቱ ችሎ ገልጿል ።

ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ላይ የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ፣ የኢንጂነሪንግ እና የሒሳብ ማዕከላትን (STEM Center) ለማቋቋም እንቅስቃሴ ለማስጀመር የኮምፕዩተር ድጋፍ ለትምህርት ቤቶች ማድረጉ የሚታወስ ነው።

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.