በመቱ ዩኒቨርሲቲ የስነምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ከፌዴራል የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር አካሄደ፡፡

የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድሩ የተካሄደው ባለፉት 20 አመታት ኮሚሽኑ ሙስናን በመከላከል ረገድ የሰራቸውን ስራዎች በህብረተሰቡ ዘንድ በተለይ ለተማሪዎች ግንዛቤ ለማስጨበጥ ነው፡፡

በዚሁ መሰረት ኮሚሽኑ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር የተካሄደ ሲሆን ከተወዳዳሪ ተማሪዎችም አብላጫ ነጥብ ያመጡ ሁለት ተማሪዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የጥያቄና መልስ ውድድር ተሳታፊ እንደሚሆኑ ለመረዳት ተችለዋል፡፡

የመቱ ዩኒቨርሲቲ የስነምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ ፅጌ በጥያቄና መልስ ውድድሩ ላይ እንደተናገሩት  የፌዴራል የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ላለፉት 20 አመታት ሙስናን ለመከላከል የሰራቸው ስራዎች የሚያበረታታ ቢሆንም ከዚህ የተሻለ ለመስራት የሁሉም ዜጋ ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህም ይረዳ ዘንድ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በተለያዩ መንገዶች እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ተማሪዎች ለስነ ምግባር ጉዳይ ትልቅ ትኩረት እንዲሰጡ እድል ከመፍጠሩ ባሻገር የኮሚሽኑ ዋነኛ ተልዕኮ የሆነዉ የስነ ምግባር ግንባታ ሥራ በሁሉም ዘርፍ ግንዛቤ እንዲኖር ያግዛል ብለዋል፡፡

ተማሪዎቹም በውድድሩ ጥሩ ፉክክር  እንዳደረጉ ገልጸው፤ ለስነ ምግባር ጉዳይ ትልቅ ትኩረት እንዲሰጡ እድል ከመፍጠሩ ባሻገር ግንዛቤ በውስጣቸው እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል፡፡

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.