በመቱ ዩኒቨርሲቲ የበደሌ የግብርናና ደን ሳይንስ ኮሌጅ የ2013 ዓ.ም የአንደኛ ሩብ አመት የሥራ እቅድ አፈፃፀም ለኮሌጁ ማህበረሰብ አቀረበ።
ዛሬ ህዳር 1/2013 ዓ.ም የበደሌ ግብርና እና ደን ሳይንስ ኮሌጅ የመቱ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራር አባላት፣ የኮሌጁ ማህበረሰብና የአከባቢዉ ማህበረሰብ ተወካዮች በተገኙበት የ2013 ዓ.ም የአንደኛ ሩብ አመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርቧል።
በዝሁ መድረክ በ2012 ዓ.ም በኮሌጁ የተሻለ የሥራ አፈፃፀም ላሳዩ የሥራ ክፍሎችና ኮሌጁን ሲደግፉ ለነበሩ አጎራባች ቀበሌዎች የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጧል። በዝሁ መሠረት ከአካደሚክ ክንፍ የAnimal Science እና Agro-Economics ት/ት ክፍሎች በት/ት ጥራት ባሣዩት አፈፃፀም፣ ከአስተዳደር ዘርፍ ጠቅላላ አገልግሎት፣ምግብ ቤት እና መዝገብ ቤት በችግርጊዜም እርፍት ጊዜያቸዉን ጭምር መስዋዕት በማድረግ ኮሌጁን በማገልገል፣ከአጎራባች ቀበሌዎች የደበና ደሩ እና የቴባ ጨበሊ ቀበሌዎች ከኮሌጁ ጋር ተቀናጅቶ በመሥራት የምሥጋና የምሥክር መረቀት ተሰጧቸዋል። በመጨረሻም የመቱ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር እንደገና አበበ የወደፊት የሥራ መመርያ ሠጠዉ መድረኩን ቋጭተዋል።

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.