ነሐሴ 16/2013 ዓ.ሞ

በመቱ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ መማር ማስተማር ጎን ለጎን የማህበረሰብ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ገለጽ፡፡

መ/ር አክሊሉ ሰይፉ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የአካዳሚክ ም/ዲን እንደተናገሩት ዋነኛው የኮሌጁ የትኩረት መስኮች የማህበረስብ አገልግሎት መስጠት መሆኑን ገልፀው ፣ በኮሌጁ ስር የሚገኙትን ስድስት /6/ የትምህርት ክፍሎች ምሁራን በማሳተፍ ችግር ፈቺና ውጤታማ የሆኑ ጥናትና ምርምሮችን በማካሄድ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች መሰራቱን መሰራቱን ገልፀዋል፤ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ስር በተለያዩ የትምህርት መስኮች ጥሩ ስራዎችን መስራታቸውን የጠቆሙ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በዋናነት በአነስተኛና ጥቃቂን ኢንቴርፕራይዝ ለተደራጁ ወጣቶች ስልጠናዎችን በመስጠት የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ስራ መሰራቱን ተናግረው ፣ በቀጣይ አመትም ይህንን ተግባር ትኩረት ሰጥቶ በመቀጠል ወጣቶች የስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ትኩረት በማድረግ እና በሌሎች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉትን ስራዎችን ለመስራት ማቀዳቸውን ገልጽዋል፡፡

ህዝብና ውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.