ህዝብና ውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ሰኔ 28/2013ዓ.ም
በመቱ ዩኒቨርስቲ 2013 አዲስ ገቢ ተማሪዎች ቅበላ መርሃ ግብር በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ።

የቅበላ ስነ ስርዓቱም ለሁለት ተከታታይ ቀናት የዩኒቨርሲቲያችን አማካሪ ካውንሲል፣ የዩኒቨርሲቲያችን ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራን አባ ገዳዎች የሃይማኖት መሪዎች፣የአካባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች ፣ ተማሪዎች ህብረት፣ ነባር ተማሪዎች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲያች ማህበረሠብ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች በደማቅ የቤቴሰባዊ አቀባበል የአቀባበል ስነሥርዓት ተደርገዋል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይም የአዲስ ተማሪ ወላጆች፣ ተማረመች በተገኙበት የችግኝ ተከላ መርሃግብር የተከናወነ ሲሆን ከዚያ መልስም ተጋባዥ እንግዶች፣ የተማሪ ወላጆች እና የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር እንደገና አበበ በተገኙበት ከአዲስ ገቢ ተማሪዎች ጋር በተማሪዎች ካፌ ውስጥ የምሳ ፕሮግራም ተካሂዷል።

በዩኒቨርሲቲው በ2013 ዓ.ም 3400 የሚሆኑ ተማሪዎች የተመደቡ ሲሆን በሁለቱ ቀናት የቅበላ መርሀግብርም በርካታ ተማሪዎቹ በሁለቱም ካምፖሶች እንደገቡ ለማወቅ ተችሏል።

 

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.