የካቲት 02/2015 ዓ. ም የህዝብና ውች ግንኙነት ዳሬክቶሬት
የመቱ ዩኒቨርሲቲ ያለፉት ስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ ውይይቱም የተካሄደው በዚህ ኣመት ሊሰሩ ከታቀዱት ውስጥ ባለፉት ስድስት ወራት የተሰሩትን ላይ ያተኮረ ሲሆን ይህንን ሪፖርት ያቀረቡትም የመቱ ዩኒቨርሲቲ የዕቅድና በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት የሆኑት አቶ ኢሳያስ ላቀውናቸው፡፡ አቶ ኢሳያስ የዩኒቨርሲቲውን የባለፉት ስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ባቀረቡት ሪፖርትም ማብራሪያ ሰትተዋል፡፡
የመቱ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በውይይቱ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩትም በዚህ ግማሽ ዓመት የተገኘው ውጤት የሁላችን የስራ ውጤት ነው ብሏል፡፡ ባለፉት ስድስት ወራት መልካም አፈጻጸም ያላቸው ክንውኖች እንዳሉ ተንጠባጥው በቀሩት ስራዎች ላይ ትኩረት ተደርገው ከቀሪው ስድስት ዋረት እቅድ ጋር ተጣጥመው መሰራት አለበት ብለዋል፡፡ አክለው በዓመት አዲስ የሚንቀበላቸው ተማሪዎችና የተመራቂ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ተፈና ላይ ሁሉም በትኩረት እንዲሰራ አስገንዝበዋል፡፡
በዚህ የስድስት ወራት ሪፖርት ውይይት ላይ ምክትል ፕሬዚዳንቶች ጨምሮ የኮሌጅና የት/ቤት ዲኖች፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች ዳሬክቶሬቶችና ቡድን መሪዎች ተገኝቶ ሰፊ ውይይት ተደርገዋል፡፡

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.