ሐምሌ 15/2013 ዓ,ም
በዩኒቨርሲቲዉ የተሰሩት የጥናትና ምርምር ውጤቶች አመርቂ ውጤት አስመዝግበዋል ተባለ፡፡
===================================================
የምርምር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የትኩረት መስኮችን በመለየት ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናትና ምርምሮችን ከ2005-2013 ዓ.ም ጀምሮ እያካሄደ ያለ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የምርምር ስራዎቹ ከዩኒቨርሲቲዉ እና አጋር ድርጅቶች MELCA- Ethiopia፣ IFS፣ Addis Ababa University፣ MELCA-Ethiopia፣ JHPIEGO ከተባሉ ድርጅቶች በተገኘ በጀት የተካነወኑ ስራዎች ውጤታማ ናቸው ተብሏል፡፡
በዚሁ መሰረት የመቱ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ሰለሞን ታደሠ ባስተላለፉት መልእክት ባሳለፍናቸዉ ዘጠኝ አመታት 39,421,931(ሰላሳ ዘጠኝ ሚሊዮን አራቴ መቶ ሀያ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰላሳ አንድ ብር) በመበጀት በሰባት ኮሌጆች ማለትም ማህበረስብ ሳይንስና ስነሰብ ኮሌጅ፣ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ፣እንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ፣ማህበረሰብ ጤና እና ሜዲካል ሳይንስ ኮሌጅ፣ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ፤ግብርናና ደን ሳይንስ ኮሌጅ ስር 511(አምስት መቶ አስራ አንድ) ጥናትና ምርምሮች የተካሄዱ ሲሆን 1,525 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ሀያ አምስት) ተመራማሪዎች ተሳትፈዋል ብለዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲዉ በቀጣይም 2014 ዓ.ም የትኩረት መስኮችን ለይቶ የጥናት ምርምሩን ስራ አጠናክሮ እየሰራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከከፍተኛ የትምሀርት ተቋመት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ከሀገር በቀል ድርጅቶች ውስጥ MELCA-Ethiopia፣IFS እና JHPIEGO በትብብር እየሰራ መሆን በተጨማሪ ገልፀዋል፡፡
ህዝብና ዉጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.