መቱ ዩኒቨርሲቲ በፋይናንስ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ዙሪያ ላይ ከተለያዩ የስራ ክፍሎች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡
ከገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ከመጡት የፋይናንስ ከፍተኛ ባለሙያ ጋር በተደረገው ውይይት ዩኒቨርሲቲው በመመሪያ 51/2010ዓ.ም በፋይናንስ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ዙሪያ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ ዳሰሳ የተደረገ ሲሆን ፤በዚህም ዩኒቨርሲቲው እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይነትም የማህበረሰቡ እና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ማሰደግና የፋይናንስ መረጃዎችን የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ለህብረተሰቡ ይፋ ማድረግ እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡ ይኸንንም የፋይናንስ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ከግብ ለማድረስ የሚመለከታቸው ክፍሎች ወቅታዊ መረጃን ለህብረተሱቡ ለማድረስ ተግተው መስራት እንዳለባቸው ተጠቁሟል፡፡ በውይይቱ ማጠቃለያም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር እንዳሉ ሙላቱ ዩኒቨርሲቲው በፋይናንስ ግልፀኝነትና ተጠያቅነት ላይ እየሰራ ያለውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ሃሳባቸውን የሰጡ ሲሆን በውይይቱም የተነሱ ገንቢ ሃሳቦችን እንደ ግብዓትነት በመጠቀም በቀጣይነት የተሻለ አሰራር ለመዘርጋት የበኩላቸውን ጥረት እንዲሚያደርጉ አስታውቋል፡፡