አስቸኳይ ማስታወቂያ

በ2012 ዓ. ም ትምህርት ዘመን በተለያ ምክንያቶች 1ኛ ሴሚስቴር ትምህርታቸውን ሳታጠናቅቁ አቋርጣው የወጡ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታችሁ እንዲመለሱ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል፡፡ በዚሁ መሰረት በመቱ ዩኒቨርሲቲ በ2012 ዓ.ም ትምህርት ዘመን በተለያዩ ምክንያቶች 1ኛ ሴሚስቴር ትምህርታችሁን ሳታናቅቁ አቋርጣችሁ የወጣችሁ በእና በአሁኑ ጊዜ ትምህርታችሁን መቀጠል የሚትፈልጉ የቅድመ-ምረቀ ተማሪዎች በሙሉ፡-

  1. በ2012 ዓ.ም ትምህርት ዘመን 1ኛ ዓመት የነበራችሁና የ1ኛ ሴሚስቴር ትምህርታቸውን ሳታጠናቅቁ አቋርጣችሁ የወጣችሁ ተማሪዎች በ2013 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ወደ መቱ ዩኒቨርሲቲ ለሚመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥሪ ስደረግ ሪፖርት እንድታደርጉ፤
  2. በ2012 ዓ.ም ትምህርት ዘመን 2ኛ ዓመት የነበራችሁና የ1ኛ ዓ.መት ሴሚስቴር ትምህርታቸውን ሳታጠናቅቁ አቋርጣችሁ የወጣችሁ ጥር 6-7/2013 ዓ. ም፤
  3. በበ2012 ዓ.ም ትምህርት ዘመን 3ኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ የነበራችሁና የ1ኛ ሴሚስቴር ትምህርታችውን ሳታጠናቅቁ አቋርጣችሁ የወጣችሁ ተማሪዎች መጋቢት 27-28/2013 ዓ.ም በአካል በመገኘት ለትምህርት ክፍላችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

በተጨማሪም

Ø  በ2012 ዓ.ም ትምህርት ዘመን 2ኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ የነበራችሁና የ1ኛ ሴሚስቴር ትምህርታችሁን አጠናቃችሁ እስከ አሁን ተጠርታችሁ ወደ ዩኒቨርሲቲው ያልገባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 19-20/2013 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በቀኑ በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

Ø  በ2013 ዓ.ም የ4ኛ ዓመት የመካኒካልና ሲቪል ምህንድስና ትምህርት ክፍሎች የነበራችሁ ልትወጡ ተቋም ያዘጋጃችሁ(የመረጣችሁ) ተማሪዎች በመረጣችሁ ተቋም ተግኝታችሁ የተግባር ልምምድ እንድትጀምሩና ከ03-07/2013 ዓ.ም ለየትምህርት ክፍሎቻችሁና ለአማካሪ መምህራኖቻችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

የመቱ ዩኒቨርሲቲ ሬጅተራር ዳይሬክቶሬት

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.