የመቱ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል ተማሪዎችን መልሶ የመቀበል ሥራ ላይ እየተወያየ ነዉ።
በcovid 19 ወረርሽኝ ምክንያት ተማሪዎች ወደየቤተሰቦቻቸው መሸኘታቸዉ ይታወሳል። አሁን ግን ወረርሽኙን ከመከላከል ስራ ጎን ለጎን የትምህርት ስራዉን ማስቀጠል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የምክክር መድረኩ ተዘጋጅቷል።
የዉይይት መድረኩን የመሩት የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር እንደገና አበበ እና የኢሉ አባቦር ዞን ዋና አስተዳዳሪና የዩኒቨርሲቲዉ ቦርድ ም/ሰብሳቢ አቶ ታሪኩ ነጋሽ ሲሆኑ ዶክተር እንደገና ለዉይይቱ መነሻ ፅሁፍ አቅርበዉ ዉይይት እየተደረገበት ይገኛል።
በመነሻ ጽሁፉ አምና ያገጠሙ ችግሮችና መንስኤያቸዉ የተዳሰሱ ሲሆን ጥልቅ ዉይይት ከተደረገባቸዉ በኋላ የቦርድ ም/ሰብሳቢዉ የስራ አቅጣጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።