መቱ ዩኒቨርሲቲ (የህዝብና ውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት) መስከረም 08/2015ዓ.ም
ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሚተገበረው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሩቃን የመውጫ ፈተናን በተመለከተ የምክክር መደረክ ተካሄደ።
መቱ ዩኒቨርሲቲ በ2015ዓ.ም ለሁሉም ተመራቂ ተማሪዎች የሚሰጠውን የመውጫ ፈተናን በተመለከተ ከትምህርት ሚኒስትር ጋር በመተባበር “የመውጫ ፈተና ለትምህርት ጥራት ያለው አስተዋጽኦ” በሚል መርህ ሃሳብ የምክክር መድረክ አካሄደ።
የምምክር መድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመቱ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ለታ ዴሬሳ እንዳሉት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በሀገር ደረጃ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አውስተው ከሚከናወኑ ተግባራት መካከልም በዚህ የትምህርት ዘመን የሚተገበረው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና አንዱ መሆኑን የገለፁ ሲሆን የዚህ የመውጫ ፈተና ዋና ዓላማ ምሩቃን በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ያገኙትን እውቀት ፣ክህሎትና የተስተካከለ አመለካከት በስራው ዓለም ብቁ ፣ተወዳዳሪ ፣በራስ የሚተማመኑ፤ ስራ ፈጣሪና አዲስ እውቀት አፍላቂ ሆነው እንዲወጡ ለማስቻል መሆኑን ተናግሯል፡፡
ዶ/ር ለታ አክለውም የምክክር መድረኩ መዘጋጀት የዩኒቨርሲቲው ባለድርሻ አካላት መምህራንና ሌሎች በ2015 ዓ.ም ለሚተገበረው የተማሪዎች መውጫ ፈተና ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና በቀጣይ ለተግባራዊነቱ የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማድረግ ነው ብለዋል፡፡
ምክክር መድረኩ ላይም የመውጫ ፈተናው መመሪያ እና አስፈላጊነት ፣ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ መሳሪያዎች፣ ከዚህ ቀደም የተሰሩ ስራዎችን መነሻ ያደረጉ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በምክክር መድረኩም ከትምህርት ሚኒስቴር የመጡ የስራ ኃላፊዎች ፣ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲ አመራሮችና ተመራማሪዎች፣፣ የመቱ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ፣ የኮሌጅ ዲኖች ፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች ፣ መምህራኖችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል፡፡
Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.