ሐምሌ 13/2013 ዓ. ም
ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደራጀው የመቱ ዩኒቨርስቲ የኤሌክትሪካል ምህንድስና ትምህርት ክፍል ቤተ ሙከራ አገልግሎቶ መስጠት ጀመረ።
መቱ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር በእጅጉ የሚያግዝ የኤሌክትሪካል እንጂነሪንግ ትምህርት ክፍል ቤተ ሙከራ ተደራጅቶ አገልግሎቶ መስጠት ጀመረ፡፡ አሁን ወደ ስራ የገባው ቤተ ሙከራ በትምህርት ክፍሉ የሚሰጡትን ዩኒቨርሲቲያችን ከዚህ በፊት ለተግባር ልምምድ ሲባክን የነበረውን ጊዜ፣ የሰው ጉልበትና ገንዘብ እንደሚያስቀርና ዩኒቨርሲተውን ድረጃውን የጠበቀ ቤተ ሙከራ ካላቸው ዩኒቨርሲቲዎች የተሻለ ቤተ ሙለራ እንዲኖረው የሚያደርግ ነው ተብሎ ይገመታል፡፡ መ/ርት አያንቱ ዳንኤል የመቱ ዩኒቨርሲቲ የእንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ዲን እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው በተለይ በኢንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጂ የተሟላ ቤተ ሙከራ ባለመኖሩ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ለመክፈትም ሆነ በመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን ለማስተማር ጫና እንደ ነበረባቸው ገልጸው፤ በዛሬው ዕለት ስራውን የጀመረው ቤተ ሙከራ ተማሪዎችም ሆኑ መምህራን ከመማር ማስተማር በተጨማሪ የተለያዩ የምርምር ስራዎችን ለመስራት ወደ ሌላ ተቋም በመሄድ የሚያወጡት ገንዘብና ጊዜ እንደሚቆጥብላቸውና ጥራቱን የጠበቀ የመማር ማስተማር ስራ ለማስተማር እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡ መ/ርት አያንቱ እንዳሉት ከረጅም ጊዜ ትግል በኋላ እውን የሆነው ይህንን ቤተ ሙከራ የማደራጀት ስራ በዕቅድ ከተያዙት አምስት ቤተ ሙከራዎች ማለትም የኤሌትሪካል፣ የሲቪል፣ የመካኒካል፣ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ማኔጂመንትእና ኬሚካል እንጂነሪንግ ትምህርት ክፍሎች ለመደራጀት ከተሰሩት ስራዎች አንዱ ሲሆን ቀሪዎቹ በቅርቡ ተደራጅተው ወደ ስራ ይገባል ብለዋል፡፡ አሁን ስራውን የጀመረው ቤተ ሙከራም በውስጡ የፓዎር፣ የኮሙኒኬሽንና የኮንትሮል ትምህርት ዘርፎችን ያጠቃለለ ሶስት ክፍሎች ያሉት ሲሆን በአጠቃልይ በኮሌጁ ቤተ ሙከራዎችን ለመደራጀት ከ150 ሚሊዮን ብር በላይበጀት ተይዞ እየተሰራ መሆኑን አክለው ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም መ/ር ፍሬው ደረጅ የኤሌክትሪካል እንጂነሪንግ መምህርና የኮሌጁ አስተዳደር ገዳዮች ምክትል ዲን እንደተናገሩ ተማረን ማስመረቅ ብቻ ሳይሆን ተማሪ ከስራ ፈላጊነት ስራ ፈጣሪ እንዲሆን የካበተ ልምድ ኑሮዋቸው ወደ ገበያ እንዲወጡ ያግዛቸዋል ብለዋል፡፡ ከዚህ በፊት የገቡት የቤተ ሙከራ እቃዎች ደረጃቸውን የጠበቁ እንዳልነበሩ የተሟሉ ባለመሆናቸው በትምህርት ላይ ችግር ሲፈጥር ቆይተዋል ብለዋል፡፡ ዕቃዎቹም ሲገዙ የዩኒቨርሲቲው ባለሙያዎች ተሳትፎበት የተገዙ ሳይሆን ቀጥታ በወቅቱ በትምህርት ሚኒስቴር ተገዝተው የቀረቡ በመሆናቸውና ብዙ ክፍሎቻቸው ባለመሟላታቸው እንደማስተማሪያነት ለመጠቀም ያስቸግር ነበር ነው ያሉት መምህር ፍሬው በሰጡን አስተያየት፡፡
ዶ/ር ለታ ዴሬሳ የመቱ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት በሰጡን አስተያየትም ዩኒቨርሲቲው ከዚህ በፊት ተማሪዎችን ለቤተ ሙከራ ትምህርት እንዲያገኙ ወደ ሌላ ተቋም መላኩ በዩኒቨርሲቲው ስራ ላይ ከፍተኛ ጫና ሲያሳድር የቆየ መሆኑን ገልጸው ይህንን ችግር ለማስቀረትም በዚህ ዓመት ባለን አቅም ሁሉ በዩኒቨርሲቲው ቤተ ሙከራዎችን ለመደራጀት ዕቅድ ተይዘው እየተሰራ ነው፡፡ ብለዋል፡፡ በቅርቡ የሲቪል፣ የመካኒካል፣ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ማኔጂመንት፣ ኬሚካል እንጂነሪንግ፣ ነኬሚስትሪ እና በሌሎች ትምህርት ክፍሎች እንደዚሁ ብዙ ገንዘብ ወጪ በማውጣት የማደራጀት ስራ ተሰርቶ ተማሪዎችን ወደ ሌላ ተቋም በመላክ ስባክን የነበረውን ጊዜ፣ ጉልበትና ገንዘብ በማስቀረት የጥራቱን የተበቀ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ስራ ይሰራል፡፡ ይህ ደግሞ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ልከፍታቸው ያሰባቸውን የሁለተኛና የአንደኛ ዲግሪ የትምህርት ክፍሎች ላይ ለመስራት ያግዛል ብለዋል፡፡
የቤተ ሙከራው አጠቃቀም ለትምህርት ክፍሉ መምህራንና የቤተ ሙከራው ቴክኒሽያኖች ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
    ህዝብና ውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.