ነሐሴ 06/2013 ዓ.ም
የህዘብና ውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
የመቱ ዩኒቨርሲቲ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2013 ዓ.ም ትምህርት መዝጊያ ሥነ-ሥርዓት በደማቅ ሁኔታ አካሄደ፡፡
የመቱ ዩኒቨርሲቲ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በዛሬው ዕለት የ2013 ዓ.ም ትምህርት የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት አካሄደ፡፡ የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓቱን ፕሮግራም ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመቱ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር እንደገና አበበ እንደተናገሩት፤ ትምህርት በተስተካከለ መስመር እንዲሄድ እንዲሁም በሳይንስና ቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን በዞኑ ውስጥ ካሉት የተለያዩ ት/ቤቶች ጋር ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰሩ እንዳለ የገለፁ ሲሆን ከዚህም ጋር በተያያዘ የመቱ ዩኒቨርሲቲ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተቋቁሞ በዞኑ ከተለያዩ ወረዳ የተወጣጡ ተማሪዎችን አወዳድሮ በመውሰድ በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ መማር ማስተማሩን እንደ ጀመረ ጠቅሰው ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቱም የራሱን ህንጻ ለመገንባት የዲዛይን ስራው ተጠናቆ በቅርቡም ወደ ስራ እንደሚገባ ጠቀሰዋል፡፡
በመዝጊያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይም የተማሪ ወላጆች፣ ከኢሉ አባቦር ዞን አስተዳደርና ትምህርት ጽ/ቤት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው የበላይ አመራሮችና አንጋፋ መምህራን የተገኙ ሲሆን የህይወት ተሞክሯቸውን ለተማሪዎች አካፍሏል፡፡ በዕለቱም የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር በመምህር አበበ ታደሰ ለተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን፡ በፕሮግራሙ ማብቂያ ላይም የዕለቱ የክብር እንግዳ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት በመስጠት የመዝጊያ ንግግር አድርገዋል፡፡
የመቱ ዩኒቨርሲቲ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በ2013 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በቁጥር 41 የሚደረሱ ተማሪዎችን በኢሉ አባ ቦር ስር ካሉ የተለያዩ ወረዳዎች አወዳድሮ በመቀበል በዋናው ግቢ እያስተማረ ያለ መሆኑ ይታወሳል፡፡

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.