ከመቱ በ20km ርቀት ላይ በጎሬ ከተማ ማስተማሪያ ሪፈራል ሆስፒታል ለማስገንባት የመጀመሪያ የዲዛይን ስራ እንዲቀርብ ተደረገ ፡፡
መቱ ዩኒቨርሲቲ በ20 km ርቀት ላይ በሚገኘው 96 ሄክታሪ በሚሆን ቦታ በጎሬ ከተማ ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ በሚሆን ወጪ በአራት ምዕራፍ ሪፌራል ሆስፒታል ለመገንባት የሚያስችል የመጀመሪያ የዲዛይን ስራ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የዩኒቨርሲቲው አመራር አባላት፣ ለምሁራን እና ለአሌ ወረዳ አመራሮች ቀርቦ ወይይት ተደረገ፡፡
በዚህ ውይይት ላይ የተገኙት የመቱ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶ/ር እንደገና አበበ እንደተናገሩት ሆስፒታሉ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥ የሚጠናቀቅ መሆኑን ገልፀው፤ አሁን ላይ በዞኑ ህብረተሰቡን እያገለገለ ያለው ሁለት ሆስፒታሎች ብቻ በመሆኑ ህብረተሰቡ በቂ አገልግሎት እያገኘ እንዳልሆነ በመናገር፣ በዩኒቨርሲቲው የሚገነባው ሆስታል ለማህበረሰቡ በቂ የህክምና አገልግሎት መስጠት የሚችልና በበቂ ሁኔታ ዕቃዎቹ የተሟላለት ሆስፒታል በማድረግ በቅርብ ርቀት ላይ ዞኖችና ለአጎራባች ክልሎች ለደቡብና ለጋቤላ ክልል ጭምር የሚያገለግል ሆኖ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የሚገነባው ሆስፒታል ለማስተማሪያነት የሚያገለግል በመሆኑ የተማረ የሰው ኃይል እጠረት ከመቅረፍ አንጻር ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ለመረዳት ተችልዋል፡፡
ለሆስፒታሉ የግንባታ ቦታ ከጎሬ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ ዩኒቨርሲቲው መረከቡ ይታወሳል፡፡