ነሐሴ 24/2013 ዓ.ም
የመቱ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች፤ወጣቶችና ልዩ ፍላጎት ዳይሬክቶሬት ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች የህይወት ክህሎት ስልጠና ሰጠ፡፡
የመቱ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች፤ወጣቶችና ልዩ ፍላጎት ዳይሬክቶሬት በዩኒቨርሲቲው በ2013 ዓ.ም አዲስ ተመድበው በትምህርት ላሉ ተማሪዎች ለሁለት ተከታታይ ቀናት በተለያዩ ርዕሶች ላይ ያተኮረ የህይወት ክህሎት ስልጠና ሰጠ፡፡
የሴቶች፤ወጣቶችና ልዩ ፍላጎት ዳይሬክተር መምህርት አባይነሽ መረባ በስለጠናው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት በ2013 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ተመድበው ለገቡት ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ስኬታማ እንዲሆኑ እና የመጡበትን ዓላማ ሳይዘናጉ ከግብ እንዲያደርሱ ተማሪዎቹ ትኩረታቸውን በትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያደረጉ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ይህን በህይወት ክህሎት ላይ ያተኮረ ስልጠና መስጠትም ለተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው አዎንታዊ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉ ለተማሪዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ስልጠናውም በተማሪዎች የህይወት፣የመጀሪያ ደረጃ የጤና እርዳታ አሰጣጥ፣የስነ ልቦና እና የማህበራዊ ህይወት አኗኗር ክህሎት ዙሪያ ላይ ያተኮረ በዘርፉ ክፍተኛ ልምድ ባላቸው መምህራን ለተከታታይ ሁለት ቀናት እንደተሰጠ ለማወቅ ተችሏል ፡፡
ዩኒቨርሲቲው በ2013 ዓ.ም ከ 3000 በላይ ተማሪዎችን ሰኔ 28-29/2013 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ተቀብሎ በመቱ ከተማ በሚገኘው በዋናው ግቢ እና በደሌ በሚገኘው የበደሌ ግብርና እና ደን ሳይንስ ኮሌጅ እያስተማረ ያለ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡
የህዝብና ውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.