የመቱ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ የ12 ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን በአረንጓዴውና ውብ በሆነው በመቱ ዋናው ግቢ እና በበደሌ ካምፓሱ ተቀበሎ ለማስፈተን ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ ነው።
====================================
በዩኒቨርሲቲውም ለተፈታኝ ተማሪዎች ምቹ ስፍራን ለመፍጠር በዩኒቨርሲቲው ኘሬዚዳንት ዶ/ር እንደገና አበበ የሚመራ ቡድንም በተማሪዎች መፈተኛ ክፍሎች፣ማደሪያ ህንጻዎች፣የመመገቢያ አዳራሾች እንዲሁም ሌሎች ዝግጅቶች ዙሪያ ላይም ክትትል በማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ታውቋል።
በቀጣይም በቡድኑ እየተሰሩ ስላሉት ዝርዝር ስራዎችና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንቀርባለን።
መቱ ዩኒቨርሲቲ
ማህበረሰቡን ለማገልገል የተቋቋመ!

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.