መቱ  ዩኒቨርሲቲ  ህዝብና  ውጭ ግንኙነት  ዳይሬክቶሬት  ግንቦት 17/2013 ዓ.ም

የመቱ ዩኒቨርሲቲ  ድህረ ምረቃ ት/ቤት አዲስ  ለሚጀምረው  የሁለተኛ  ድግሪ  ፕሮግራሞች ያዘጋጀውን   ስርዓተ  ትምህርት  አስገመገመ

የመቱ  ዩኒቨርሲቲ  የድህረ ምረቃ  ትምህርት  ቤት በ2014 ዓ.ም አዲስ  ለሚጀምራቸው  የሁለተኛ  ዲግሪ  የትምህርት  ፕሮግራሞች የስርዓተ  ትምህርት  ግምገማ  በበይነ-መረብ  አካሄደ፡፡

በመርሃ  ግብሩ ላይ  የድህረ ምረቃ  ት/ቤት ዲን  ዶ/ር ቶሎሳ  ፊጣ  የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ የመቱ ዩኒቨርሲቲ  የድህረ ምረቃ  ፕሮግራሞችን  ማስፋት  አስፈላጊ  ለዩኒቨርሲቲው  ማህበረሰብም  ሆነ  ለሀገር  ከፍተኛ  አሰተዋጽኦ  እንዳለው  ገልፀዋል፡፡ ከዚህ  ጋርም  ተያይዞ  በአንጅነሪንግ  ዘርፍ፣በቢዝነስ፣ በማህበራዊ  ሳይንስና  በእርሻው  ዘርፍ  በአጠቃላይ 10(አስር) የሁለተኛ ዲግሪ  ስርዓተ  ትምህርት  ፕሮጋራሞቸን  አዘጋጅቶ በውስጥ ምሁራን  ከተገመገመ  በኋላ በሙያው  የጠለቀ  እውቀት  ባላቸው  ከስድስት  የተለያዩ  ዩኒቨርሲቲዎች  የተወጣጡ  20(ሀያ) የሚሆኑ  ምሁራን  መገምገሙን  ተናግረዋል፡፡  ዶ/ር ቶሎሳ ፊጣ  አክለውም  በሚፈለጉት  ዘርፎች  የሰለጠነ  የሰው  ሀይል  በማዘጋጀት  ምርትንና  ምርታማነትን  መጨመር  እንደሚቻል  ገልፀው  ስርዓተ  ትምህርቱን  በማፀደቅ  ፕሮግራሞቹ  በአጭር  ጊዜ  ወስጥ  እንዲከፈቱና  ተማሪዎችን  ለመቀበል  ዝግጁ  እንዲሆን  አስፈላጊውን  ዝግጅትም  እንደሚያደርጉ  ተናግረዋል፡፡

በስርዓተ  ትምህርቱ  ግምገማ ላይ  የተገኙት  የዩኒቨርሲቲው  የአካዳሚክ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ለታ ዴሬሳ  እንዳሉት  ዩኒቨርሲቲው  የሶስተኛ  ትውልድ  ዩኒቨርሲቲ  እንደመሆኑ  በዩኒቨርሲቲው  ከዚህን  ቀደም  በተለያዩ  የትምህርት  ዘርፎች  የሁለተኛ  ድግሪ  ትምህርተ  እየተሰጠ  ያለ  ሲሆን  የአካባቢውን  የትምህርት  ፍላጎትና  ተደራሽነት  ከግምት ውስጥ  በማስገባት  በማህበራዊ  ሳይንስና  በቢዝነስ የትምህርት  ዘርፎች  አራት  ተጨማሪ  የትምህርት  ፕሮግራሞች  እንዲሁም  በኢንጅነሪንግርና  ቴክኖሎጂ  አምስት እና  በግብርናው ዘርፍ  አንድ  አዲስ  ሥርዓተ  ትምህርቶችን  በማዘጋጀት  ትምህርት  ለመጀመር  በዝግጅት  ላይ  መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ስርዓተ ትምህርቱን  በመስኩ  ልምድ  ባላቸው  ምሁራን  በበይነ  መረብ  በማስገምገም  ከፍተኛ  ግብዓት መገኘቱንም  ዶ/ር ለታ  ዴረሳ አክለዋል፡፡

Mettu University Public and External Relations Directorate May 17, 2013

Mettu University Postgraduate School has conducted Curriculum Review workshop for Newly Opening Post graduate Programs

MeU School of Post Graduate conducted curriculum review workshop on the newly   opening MA/Msc program in the coming academic year.

After Welcoming the program, Dean of the Graduate School, Dr. Tolosa Fita, said that expanding the postgraduate programs of the university is important for the university community and the country.  He said that, the University has prepared 10 (ten) postgraduate curriculum programs in engineering, business, social sciences and agriculture and evaluated by 20 scholars from six different universities.  Dr. Tolosa Fita added that it is possible to increase production and productivity by developing skilled manpower in the required sectors.

Dr. Leta Deresa, Academic Vice President of the University, who attended the review of the curriculum, said the university is currently offering a master’s degree in various fields of study.   Dr. Leta said that, by considering the need and accebility of education in the area, the University has prepared four additional programs in the field of social and Business fields and five new curricula in engineering and technology and one in the agricultural fields.  Dr. Leta Deresa added that the curriculum has been reviewed online by experienced scholars in the field and supportive comments have been gained.

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.