የማህበረሰብና ማማከር አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከባለድርሻ አካላት ጋር የማህበረሰብ አገልግሎት ጭብጥ ትኩረት መስክ ማረጋገጫ እና የማህበረሰብ ተሳትፎ የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡
የማህበረሰብና ማማከር አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከባለድርሻ አካላት ጋር የማህበረሰብ አገልግሎት ጭብጥ ትኩረት መስክ ማረጋገጫ እና የማህበረሰብ ተሳትፎ የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡ የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብና ማማከር አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ውይይት መድረክ ያካሄደው የሚሰጠው የማህበረሰብ አገልግሎት የተጠናና የማህበረሰቡን ፍላጎት ማዕከል ያደረ እንዲሆን ነው፡፡ በዚህ የውይይት መድረክ ላይ ዩኒቨርሲቲው እስካሁን ለማህበረሰቡ እየሰጣቸውና እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን አጠቃላይ ገለጻ በመ/ር ስማገኘው መላኩ በማህበረሰብና ማማከር አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይክተር ተሰጥቷል፡፡ በገለጻቸውም ላይ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው ከተቋቋመለት ዓላማ አንጻር የተሰሩት ስራዎች የተፈለገውን ያህል ባይሆንም በግብርና፣ በኢኔርጂ፣ በጥቃቅንና አነስተኛ፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በስራ ፈጠራ በከተማ ውበትና በነጻ የህግ አገልግሎት አበረታች ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡ እንዲሁም በጅመር ላይ ያሉት ስራዎችም በተለይ ለወጣቶች ስራ እድል ከመፍጠር ዘመናዊ የዶሮ እርባታ፣ የልስትሮ ሸድና የንብ ዕርባታሌሎች ስራዎች በቅርቡ ተጠናቀው ለማህበረሰቡ አገልግሎት በስጠት ይጀምራል ነው ያሉት፡፡
በመቀጠልም ለሚቀጥሉት ዓመታት ዩኒቨርሲቲው ልሰራበቸው ጥናት የለያቸው የማህበረሰብ አገልግሎት ጭብጥ የትኩረት መስክ በተመራማሪ የዩኒቨርሲቲው መምህራን ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካህዶባቸዋል፡፡
በዚሁ መሰረት በጥናት ከተለዩት የጭብጥ የትኩረት መስኮች በየኮሌጆች ተለይተው ቀርበዋል፡፡
በዚህ የውይይት መድረክ ላይም በየደረጃው ያሉት የዩኒቨርሲቲው አመራር፣ የኢሉ አባቦርና የቡኖ በደሌ ዞኖች የተለያዩ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች፣ የሀይማኖት ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡