የስትራቴጅክ ዕቅድ ዝግጅት ላይ ከዩኒቨርሲቲው ካውንስል ጋር ውይይት ተደረገ፡፡

በመስከረም 5/1/2013 ዓ.ም ከዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባለት ጋር ባደረገው የ10 አመት የዩኒቨርሲቲው ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ውይይት ስደረግ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት በሰጠው የመነሻ ዕቅድ መሰረት በማድረግ የአካዳሚክ ልህቀትን ለመጨመር፤ የጥናትና ምርምር፣ የማህበረሰብ አገልግሎትና ተሳትፎ፣ የመልካም አስተዳደርና የአሰራር ልህቀት ያካተተና የዩኒቨርሲቲውን መሪ ቃል የቃኜ መሆን እንደሚገባ በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡ዶ/ር እንደገና አበበ የመቱ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እንደተናገሩት የከዚህ በፊቱ ስትራቴጅክ ዕቅድ የዩኒቨርሲቲውን መሪ ዕቅድ ምን ያህል እንዳሳካ ያለፉት ዓምስት ዓመታት ስትራቴጅክ ዕቅድ ግምገማ መታየት እንዳለበትና አሁን የሚዘጋጀው ዕቅድ ከዚህ በፊት ከተዘጋጁት መነሻ በማድረግ የነበሩትን ጠንካራና ደካማ ጎኖቻችን በግምገማ ተለይተው ዩኒቨርሲቲው ወደፊት አሳክቶ ሊደርስበት የሚችልበት ቦታ የሚያሳይ ለማድረግ የተለያዩ ኮሚቴዎች ተዋቅረው ስትራቴጅክ ዕቅዱ በትኩረት እንዲዘጋጅ የሚቋቋሙ ኮሚቴዎችም በአፅንኦት እንድሰሩ አሳስበዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አዲስ ተጠንተው የተፈቀደው የዩኒቨርሲቲው የኮሌጅ መዋቅር በየደረጃው ለሚገኙት የአመራር አካላት ቀርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በዚሁ መሰረት ከዚህ በፊት በፋካልቲና በተቋም ደረጃ ተደራጅተው የነበሩት ወደ ኮሌጅ ያደጉ ሲሆን የህግ ት/ቤት በነበረው እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል፡፡ አዲስ በጥናት የተፈቀደው መዋቅርም ኃላፊነትን ወደ ታች ከማውረድ በተጨማሪ ተጨማሪ የስራ ዕድሎችን ለመፍጠር እንደሚረዳ ከተሰጠው ከገለፃ ለማወቅ ተችሏል፡፡ዩኒቨርሲቲው ባለፉት አመታት የኮሌጅ መዋቅር ባለመደራጀቱ በሚሰጠው አገልግሎቶች ላይ ወጥነት ያለው ስራ ለመስራት እንፋት ሆኖ መቆየቱ አንስተው፤ አሁን በተደረገው የኮሌጅ አደረጃጀት ሲነሱ የነበሩትን ችግሮችን መቅረፍ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.