ህዳር 20/2015 ዓ.ም. (ህዝብና ውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት)
መስናን መታገል በተግባር በሚል መሪ ሀሳብ ዓለም ዓቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በመቱ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ።
የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ለተሳታፊ እንግዶች ያስተላለፉት የዩኒቨርሲቲው የፀረ ሙስና እና ስነ ምግባር መከታታያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንደገለፁት የበዓሉ ዓላማ በዓሉን ምክንያት በማድረግ በዩኒቨርሲቲው የፀረሙስና ችግሮችን ለመፍታት እንዲቻል የተቋሙ ህ/ሰብ በፀረሙስና ትግሉ ሚናውን እንዲወጣ፣ በባለቤትነት ጠንክሮ እንዲታገልና ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ እንዲሁም ግንዛቤ በመፍጠር በፀረ ሙስና ትግሉ ህዝባዊ ንቅናቄና መነሳሳት እንዲፈጠር ለማደረግ ነው ሲሉ ገልጿል።፡፡
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመቱ ዩኒቨርሲቲ የፕሬዝዳንት ተወካይ እና የአስ/ተማ/ጉ/ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተካልኝ ቀጄላ በመድረኩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክትም “ለአገራችን ህዝቦች ልማት፣ ዕድገትና ሰላም እየደረሰ ላለው ሁሉ አቀፍ እንዲሁም የስነ ምግባር ብልሹነት ትውልድ ላይ የሚያደርሰው የሞራል ውድቀት የአገርንና ህዝብን አደራ በታማኝነት አለመወጣት ለአገራችን ሁለንተናዊ ዕድገት ፀር መሆኑን ተገንዝበን ሁሉም የስነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ መታገል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የዓለም የፀረ ሙስና ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ ጊዜ በኢትዮጳያ ደግሞ ለ18ኛ ጊዜ ነው የተከበረው፡፡
በመድረኩ ላይም የተለያዩ ጥናታዊ ዕሑፎች ቀርበው ሰፊ ውይይቶች ተደርጎባቸዋል።

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.