የዓለም የፀረ ሙስና ቀን በፓነል ውይይት ተከበረ፡፡
የዓለም የፀረ ሙስና ቀን የትውልድን የስነ ምግባር ግንባታን በጠንካራ ዲሲፕሊን በመምራት ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን በመታገል የብልጽግና ጉዞችንን እናፋጥናለን በሚል መሪ ቃል በፓናል ውይይት ተከበረ፡፡ የዩኒቨርሲቲያችን አካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ለታ ዴሬሳ በፓናል ውይይቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ሙስና በባህርይው ውስብስብ በመሆኑ የአንድን ሀገር ማህበራዊና ፖለቲካዊ ከመጉዳቱ በተጨማሪ ለዜጎች የሰላም ዕጦትና አለመረጋጋት ዋነኛው መንስኤ ነው ብለዋል፡፡ በዚህ የፓነል ውይይት ላይ የመወያያ ፅሑፍ ያቀረቡት የዩኒቨርሲቲያችን የህግ ት/ቤት የሆኑት መ/ር ዳኜ ጀንበሬ ሲሆኑ ባቀርቡት ፅሑፍም ሙስና በሀገር ላይ የሚያደርሳቸው ተፅዕኖ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ፤ የሰላም ዕጦትና አለመረጋጋት፤ የህግ የበላይነት መሸርሸር፤ መሰረታዊ የሰብአዊ መታጣትና ነፃነቶች መጣስ እና የዜጎች ፍትሀዊ መጓደል ልያስከትል ይችላል ብለዋል፡፡ በቀረበው ፅሑፍ ላይ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርገዋል፡፡ በፓነል ውይይቱ ላይ ዩኒቨርሲቲያችን አመራሮች፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና መምህራን ተሳትፈዋል፡፡