በመቱ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች፣ ወጣቶችና ልዩ ፍላጎት ዳይሬክቶሬት የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ በማስተባበር በኢሉባበር ዞን ማረምያ ቤት ለሚገኙ የህግ ታራሚ ሴቶች የንህና መጠበቂያ የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገላቸው፡፡

ድጋፉ የተደረገላቸው በኢሉባቦር ዞን ማረምያ ቤት ለሚገኙ የህግ ታራሚ ሴቶች የንህና መጠበቂያ ነው፡፡ ድጋፍ የተደረገው የህግ ታራሚ ሴቶች የንህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች በዩኒቨርሲቲው የሴቶች፣ ወጣቶችና ልዩ ፍላጎት ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት ከመምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች ከተሰበሰበ በኋላ በአካል ሂደው በስፍራው በመገኘት ለ40 ለሚሆኑ ሴት ታራሚዎች ድጋፉ የተበረከተው፡፡

ረ/ፕሮፌሰር አዳነች አስፋው የመቱ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዚዳንት በስፍራው ተገኘተው ድጋፉ ሲደረግ እንደተናገሩት ሴቶች ችግሮቻችን ለመፍታት አንድ በመሆን በቅንጅት ለመስራት ትልቅ ዕድል እንደፈጠረላቸው ተናግረው፣ ድጋፉ በቀጣይነት የሚደረግላቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ድጋፍ የተደረገላቸው የህግ ታራሚ ሴቶች እንደተናገሩት በተደረገላቸው ስጦታ እንደተደሰቱ ገልጸው፣ የተሰጣቸው ድጋፍ በወሳኝ ሰዓት እንደደረሳቸው ተናግረዋል ፡፡ ድጋፉ የተሰጠው ለ40 ሴቶች ነው፡፡

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.