ውድ የመቱ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብና አካባቢው ነዋሪዎች፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ያላችሁ ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ2015 ዓ.ም አዲስ ዓመት በዓል በሰላምና በጤና ፣ አደረሰን አደረሳችሁ።
ዩኒቨርሲቲያችን በ2022 በዘመናዊ ግብርናና በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት መስኮች ፣ በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት በኢትዮጲያ የታወቀ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን ራዕይ በመሰነቅ ይህንንም ከግብ ለማድረስ መሪ ዕቅድ አዘጋጅተን እየሰራን እንገኛለን፡፡ ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠር ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ስራዎችም እየተሰሩ ነው ፡፡ ባሉንም የትምህርት መስኮች በተደራጁ ቤተ ሙከራዎችና ብቁ የሰው ሀይል የትምህርት አሰጣጥ ጥራት በማሳደግ ተመራቂዎቻችን ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እና በህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ያለውን ዘመናዊ እና ብቃት ያለውን የሰው ኃይል ለማፍራት የሚያስችል ስራዎች እየሰራን እንገኛለን፡፡
ዩኒቨርሲቲያችን ለተማሪዎቻችን የሚሰጠውን የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት በተለያዩ መርሃ ግብሮች በቅድመና ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ከማስተማርና ማሰልጠን ባሻገር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናትና ምርምር ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን፡፡
በአዲሱ ዓመትም እንደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የሚጠበቁብንን ስራዎች በመስራት ራዕይያችን በማሳካት የዩኒቨርሲቲያችን ከፍታ ዘመን እንዲሆንና ጥሩ የስራ ዘመን እንዲሆንላችሁ እየተመኘሁ በድጋሚ እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ፡፡
መልካም አዲስ አመት!
እንደገና አበበ (ዶ/ር)
የመቱ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.