የመጀመሪያ የፈጠራ ስራቸውን ጀባ ያሉት ከዛሬ 14 ዓመት በፊት በ1997 ከዩኒቨርሲቲ ተመርቀው እንደወጡና በ2ኛ ደረጃ መምህር ሆነው እንደተመደቡ በት/ቤቶች አካባቢ የሚታየው የተማሪዎች ውጤት ማጠራቀሚያ (ሮስተር) የሚሰራው በእጅ በመሆኑና ይህ ደግሞ አንድ ስህተት ስፈጠር ሁሉንም በእጅ ማስተካከል ስለሚያመጣ እንዲሁም ስራው አድካሚና ተመሳሳይ ስህተት ለመስራት መንገድ ስለሚከፍት ይህንን ችግር በአዲስ ሶፍትዌር በውስጣቸው ያለውን በቴክኖሎጂ የመጠቀምና ለሁሉም ማህበረሰብ አገልግሎት አስተዋፅኦ ያበረከቱት፡፡
የተማሪዎች ሮስተር መስሪያ ሶፍትዌሩ የመቱ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለ14 ዓመታት እየተጠቀበመት ይገኛል፡፡ በ2012 ዓ.ም ደግሞ በሁሉም የኦሮሚያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተሰራጭተው እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡ የሮስተር መስሪያ ሶፍትውሩ በተማሪዎች ውጤት አያዝ ያለውን ችግር በእጅጉ እነደሚፈታ አምናለሀው ብለዋል የፈጠራው ባለበት ዶ/ር ጋሩማ አብዲሳ፡፡
ዶ/ር ጋሩማ አብዲሳ እንዳሉት በወቅቱ የነበሩት አካላትም ለስራው እውቅና ቢሰጡም አስፈላጊነቱን አይተው የፈጠራ ስራውን አላሰራጩም ነበር ብለዋል፡፡ በመቱና በዙሪያዋ ብቻ ነበር ላለፉት ዓመታት ስጠቀሙበት የነበሩት፡፡ አሁን የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ያንን ተሞክሮ አይተው ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በሁሉም ትምህርቶች ጥቅም ላይ እንድውል አድርገዋል ብለዋል፡፡
ሌላው ይላሉ ዶ/ር ጋሩማ አብዲሳ ባለፈው ዓመት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቴክኒካል መዝገበ ቃላት የመቱ ዩኒቨርሲቲ መመህራንና የመቱ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ መምህራን በማስተባበር ሰርተን ነበር፡፡ የቴክኒካል መዝገበ ቃላቱን ወደ ሞባይል መተግበሪያ (አፕልኬሽን) ቀይሬ ጥቅም ላይ እንድውል አድርገዋለሁ ይላሉ፡፡
ይህ መዝገበ ቃላት ተመሪዎች እስከ 8ኛ ክፍል በአፋን ኦሮሞሲማሩ ቆይተው 9ኛ ክፍል ላይ በእንግልዝኛ ቋንቋ ትምህርታቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ይህ ደግሞ በአፋን ኦሮሞ ስማሩ የነበሩት ቃላት ሃሳቡን እያወቁ የሚማሩት በእንግልዝኛ ቋንቋ በመሆኑ ብቻ ችግር ይገጥማቸዋል፡፡ ስለዚህ ይህንን ችግር ለመፍታት ከሂሳብ፣ ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪና ከቋንቋ መመህራን ጋር በመጣመር የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቴክኒካል መዝገበ ቃላት አዘጋጅተናል ነው ያሉት ዶ/ር ጋሩማ አብዲሳ፡፡
ተማሪዎች በት/ቤት በሚማሩት የትምህርት ዓይነቶች ሁሉ በድጋሚ የተዘጋጀ ሲሆን ይህም ቃላቶቹ በመጀመሪያ በእንግልዝኛ ቋንቋ ከተፃፈ በኋላ ፊቺው በአፋን ኦሮሞ ከነማብራሪያው የተዘጋጀ ነው፡፡ አንድ ዓለም አቀፍ መዝገበ ቃላት ማሟላት ያለበት ሁሉ አሟልቶ ነው የተዘጋጀ ይላሉ በማብራሪያቸው ዶ/ር ጋሩማ፡፡ መዝገበ ቃላቱም በኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ በኩል ህትመቱ ተጠናቋል፡፡ በቅርቡም ለት/ቤቶች ይሰራጫል ብለዋል፡፡
አሁን ደግሞ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በመከሰቱና ህጻናት በተለይ የቅድመ መደበኛና የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ለረጅም ጊዜ ቤት በመቆየታቸውና ከትምህርት ገበታቸው በመራቃቸው ብዙ ተፅዕኖ እንድደርስባቸው የታወቀ ነው ያሉት ዶ/ር ጋሩማ ችግሩን ለመቅረፍ አንድ ሃሳብ ወደ አዕምሮዬ መጣና እኔ ሃሳቡን ወደ ተግባር ለወጥኩ ይላሉ፡፡ ይህ ችግር ለመፍታት አንድ የፈጠራ ስራ ለሁሉም ሰው በቀላሉ አድረጌ ሰራሁት ይላሉ፡፡ የፈጠራ ስራውን እንድሰራ በይበልጥ የገፋፋኝ ልጆች በቤት ውስጥ ሆኖ የሌላውን የማያውቁትን ቋንቋ በመጠቀም ቴክኖሎጂን ይማራሉ፡፡ ይህ ደግሞ ማንነታቸውን እንዲረሱ ያደርጋል፡፡ ይሄን ችግር ለመፍታት እኔ የኮሮና ወረርሽኝ መከሰትን እንደ ጥሩ አጋጣሚ በከልቻ የሚልና በሞባይል መተግበሪያ የሚሠራ የህጻናት መማሪያ ሶፍት ዌር ለመፍጠር ቻልኩ ይላሉ ዶ/ር/ ጋሩማ አብዲሳ፡፡ ሌላው ደግሞ ልጄ የቅድመ መደበኛ ተማሪ ነው፡፡ ስለዚህ ልጄን ለማስጠናት ፊደሎችን ሳስተምረው የግድ ወረቀት ላይ መጻፍ እንዲሁም መቆራረጥ ይጠበቅብኛል፡፡ ይህ ደግሞ ድግግሞሽና ጊዜዬን በብዙ ይወስድብኛል፡፡ ይህንን የራሴን ችግር ለመፍታትም ያደረኩት ጥረት ከእኔ አልፎ ለማህበረሰቡም ችግሩን እንድፈታ ያነሳሳኝ ይላሉ፡፡
ይህ መተግበሪያ በማንኛውም ጊዜ ለህጻናት በትምህርታቸው እንደ ደጋፊ(Supplementary) ያገለግላል ማለት ነው፡፡ መተግበሪያው ህጻናት በቀላሉ የአፋን ኦሮሞ፣ ሂሳብና ሳይንስ ትምህርቶችን በቀላሉ የሚማሩት መተግበሪያ ነው፡፡ የመተግበሪያው ስያሜ በከልቻ የሚል ሲሆን ስያሜውን የሰጡት ሃሳቡን የሚደግፉት ሰዎች ነው፡፡ ሶፍትዌሩ ህጻናት እንዴት አድርገው በድምፅና በምስል በመደገፍ ፊደል መማር እንደሚችሉ፣ የአፋን ኦሮሞ ሰዋሰው ህግጋትን በጠበቀ የተዘጋጀ ነው፡፡ መተግበሪያው 370 ቃላት ከነምሳሌዎች የመለፀገ ነው፡፡ ሌሎች እንዲፅፉና እንደሚነቡ ነው የሚያስተምረው፡፡ ሕጻናት በቀላሉ ቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው ሊማሩበት ይችላሉ፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ህፃናት በባህርያቸው ጨዋታን ስለሚወዱ የተለያዩ የኦሮሞ ስነቃል ማለትም ተረት ተረትና እንቆቅልሽ አለው፡፡ የቀናትና የወራት በስያሜና በፅሑፍና በድምፅ የያዘ ነው፡፡ ለወደ ፊት መተግበሪያው በይዘትና በጥራት ሌሎች የትምህርት ዓይነቶች ይዞ እንዲሻሻል ይደረጋል ብለዋል፡፡
ዶ/ር ጋሩማ እንዳሉ የትምህርት ለማስጠበቅ በቴክኖሎጂ መደገፍ አለበት፡፡ ይህ መተግበሪያ በሞባል የተዘጋጀ ከሁሉም የቴክኖሎጂ አማራጮች ሞባይል እስከታችኛው ማህበረሰብ ስለሚገኝና ቀላል በመሆኑ ነው፡፡
ይህ ቴክኖሎጂ ሲታይ ዩኒቨርሲቲዎች ከተቋቋሙበት ዓላማ አንፃር ስራው የማህበረሰብ አገልግሎት ነው የሚሉት ዶ/ር ጋሩማ አብዲሳ ይህ መተግበሪያ ከሚሰጠው ጠቀሜታ አንፃር ሃሳባቸውን ሲገልፁ ልጆችን ለማስተማር ገበያ ላይ ያሉትን ስንመለከታቸው በአፋን ኦሮሞ በቻርት እንኳ የተዘጋጀ እምብዛም በገበያ ላይ የለም ይላሉ፡፡ በወረቀትና በቻርት ደረጃ በገበያ ላይ የሌለን ጣራት ባለው ድምፅና በምስል ቀለል ባለ ቴክኖሎጂ ስያገኙ የተሸለ ነው ብዬ አስባለው፡፡ መተግበሪያውን ለአንዳንድ ሰዎች በመስጠት ጥሩ ግብረ መልስ አግኝቸበታለው ያሉት ዶ/ር ጋሩማ መተግበሪያው የተዘጋጀው በአፋን ኦሪሞ ጥሩ የትምህርት ደረጃና የማስተማር ልምድ ካላቸው የመቱ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ጋር የተዘጋጀ በመሆኑ ምንም ዓይነት ስህተት እንዳይኖረው ተደርጎ ነው ያሉት፡፡ መተግበሪያው ለገንዘብ ማግኛ የተዘጋጀ ባለመሆኑ ማንም ሰው በነፃ ሊያገኘው ብለዋል፡፡
በመተግበሪያው የተካተቱት ይዘቶች ከተማሪዎች መማሪያ ካሪኩለም የተወሰዱ በመሆናቸው ሙሉ በሙሉ የኦሮሞን ባህልና ዕሰት በሚገልፅ ነው ያሉት ዶ/ር ጋሩማ በምሳሌ ያብራሩ “A” ለማስተማር “Arba” (ዝሆን) በሚለው በድምፅና በምስል የተዘጋጀ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከተማሪዎች መማሪያ መጽሐፍ የተወሰደ ነው፡፡ በኦሮሚያ ውስጥ የህብረተሰቡ አኗኗር ገጠር፣ ከተማ፣ አርሶ አደር፣ አርብቶ አደር እና ሌሎች ማህበራዊ ስብጥር ያለው በመሆኑ ይህንን ከግንዛቤ በማስገባት ነው የተዘጋጀ ያሉት ዶ/ር ጋሩማ በኦሮሚያ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም የንግግር ዘዬ (Dialectic) እንድይዝ ተደርጎ ነው የተዘጋጀ፡፡ ለምሳሌ በኢሉ አባቦር የሚነገረውንና በቦረና ወይም ሸዋ የሚነገረውን መግለፅ በሚችል ሆኖ ነው የተዘጋጀው፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት የየአካባቢውን ባህልና ዕሰት እንድጠብቅ ተፈልጎ ነው፡፡ ብዙ ሰዎችም አስተያየት ሰጥተውበታል ብለዋል፡፡
መተግበሪያው ህብረተሰቡ ዘንድ መድረስ የሚችልበት መንግድም ስያነሱ በሁሉም የኦሮሚያ አካባቢዎችና በእያንዳንዱ ቤት ወጣትና ህፃናት አሉ፡፡ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ህብረተሰቡን ማገልገልና ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ማድረግ አለበት እሳቤው፡፡ በዋናነት ህጻናት ላይ ከተሰራና ህጻናት ማንበብና መፃፍ እየቻሉ ስመጡ ጥሩ ዜጋ የመሆን ዕድላቸው ሰፊ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጋር በቀላሉ እንድደርሱ ከተለያዩ አካላት ለምሳሌ ከኢሉ አባቦር ት/ፅ/ቤት ጋር ከየወረዳው ያሉ ፈጻሚዎች ጋር በአንድ መድረክ ላይ እንዲደርሳቸው ላገኙት ሰዎ እንድሰጡ ነው፡፡ ሌላው ከኦሮሚያ ት/ቢሮ ጋር እየተነጋገርንበት ነው ያለነው፡፡ እነዚህ አካላት በመቱ ዩኒቨርሲቲ አማካይነት ተገናኝተው ለማህበረሰቡ እንዲያደርሱ የሚል ሃሳብም አለ ይላሉ ዶ/ር ጋሩማ፡፡ ይህ ካልተሳካም በዩኒቨርሲቲውና በመቱ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ተማሪዎች አማካይነት እንዳደረስ ይደረጋል ብለዋል፡፡
ከዌብሳይትም አውርደው መጠቀም ይቻላል፡፡ ይህ መተግበሪያ ለማገኙት ማህብረሰቡ አስቀድሞ መኖሩን ማወቅ አለበት፡፡ ከዚያም ባገኘው አማራጭ ሁሉ እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡
በመጨረሻም ከባለቤትነት መብት ጋር አያይዘው ለጠየቅናቸው ስመልሱ ስራው ባለቤትነቱ የእኔ መሆኑና ከሚመለከተው አካልም የባለቤትነት መብት ማግኘት እንደሚገባኝ አውቃለው ብለዋል፡፡ ዋናው የእኔ ዓላማ ህብረተሰቡ የሚያገኘው ጥቅም ነው እርካታ የሚሠጠኝ ብለዋል፡፡ ስራው ጥቅም የሚያስገኝ ከሆነ በራሱ ጊዜና መስመር እግዝአብሔር ተጨምሮበት ይገኛል፡፡ ዋናው ቁምነገር ለሰው ሁሉ መልካምን ማደረግ ነው ዕውቅናዬ ብለዋል፡፡ ሁልጊዜ መልካም መስራትና ወጣቱን ትውልድ ማብቃት ላይ መሆን አለበት፡፡ ለሁሉም ሲያልፍ ነው ለእኔም ለልጄም ለወደፊት የሚያልፍለት፡፡
እኔ ጎረቤቴን ወይም በሚችለው ሁሉ ከረዳኋቸው በሕይወቴ ሁሉ ማየትና ማግኘት የማልችለውን ሰው ባለበት ቦታ ሆኜ መቅረፍ የሚችለውን ችግር መቅረፍ መቻሌ ይኼ ለእኔ በራሱ እንደ ዕድል እቆጥራለሁ ይላሉ ዶ/ር ጋሩማ አብዲሳ፡፡ ስለዚህ ከፈጠራ ባለቤትነት መብት ጋር ተያይዞ በቅርቡ እጨርሳለሁ፡፡ ለወደፊት የጀመርኩትና ልሰራ ያቀድኳቸው የፈጠራ ስራዎች ሃሳብ አለኝ ብለዋል በመጨረሻ ላይ በሰጡን ማጠቃለያ ሃሳባቸው፡፡
የኢሉ አባቦር ዞን ት/ጽ/ቤትም ዶ/ር ጋሩማ አብዲሳ ለሰሩት ለዚህ በጎ ስራ ዕውቅትና ሰጥቷቸዋል፡፡ይህንን መተግበሪያ Bakkalchaqubee ከሚለው የቴሌግራም ግሩፕ ላይ አውርዶ መጠቀም ይቻላል፡፡