ጥቅምት 13/2014 ዓ.ም፤ መቱ ዩኒቨርስቲ ህዝብና ውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ሲያስተምራቸው የነበሩትን ከ370 በላይ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎችን በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመረቀሲያስተምራቸው የነበሩትን ከ370 በላይ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎችን በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመረቀ::

ዩኒቨርሲቲው በጤናው ዘርፍ ያለውን የጤና ባለሙያዎች እጥረት ለመቅረፍ በትጋት እየሰራ እንዳለ የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው ዕለትም አጠቃላይ ተመራቂዎች 72 የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂዎች ሲሆኑ 135 ደግሞ ሴቶች መሆናቸው ታውቋል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር እንደገና አበበ እንደተናገሩት በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ካለባት የጤና ባለሙያዎች እጥረት አንፃር የዛሬው ተመራቂዎች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ተመራቂዎቹም በሰለጠኑበት ዘርፍ ሀገራቸው እንዲሁም ማህበረሰባቸው በሚፈልጉባቸው ቦታዎች ላይ ሁሉ በሰለጠኑበት ሙያ የሙያ ስነ-ምግባር እና የገቡትን መሃላ በመጠበቅ ህብረተሰቡን በታማኝነት ማገልገል እንዳለባቸው አሳስቧል።

በምርቃቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የጅማ የዩኒቨርሲቲ የም/ማ/አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነፃነት ወርቅነህ ባደረጉት ንግግር፤ “በዓለምና በሀገር አቀፍ ደረጃ ተንሰራፍቶ በነበረው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተስተጓጉሎ የነበረውን ትምህርት በማካከስ ለዚህ ልዩ ቀን በመድረሳችሁ እሸናፊዎች ናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ” ብለው መልዕከት አስተላልፏል። ዶ/ር ነፃነት አክለውም ዩኒቨርሲቲው በሀገር ደረጃ በጤናው ዘርፍ ያለውን የተማረ የሰው ሀይል እጥረት ለመቅረፍ እየሰራ ያለው አበረታች ስራ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ገልጿል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ማጠቃለያ ላይም በትምህርት ክፍሎች እና በኮሌጅ ደረጃ ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ ተማሪዎች የሜዳልያ እና የእውቅና ሠርተፊኬት ተሰጥቷቸዋል።

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.