ቀናት ወራትን፣ ወራት አመታትን እያስቆጠሩ፤ ፀሀይም በጨለማ፣ ወቅቶችም የተፈጥሮ ዑደታቸውን ጠብቀው እየተፈራረቁ እነሆ መቱ ዩኒቨርሲቲ ከተቋቋመ 10 ዓመት ሞላው፡፡ የዩኒቨርሲያችን ማህበረስብ፣ የአከባቢያችን ነዋረዎች፣ ዩኒቨርሲቲያችን ዛሬ ለመድረሱ በእውቅትም በክህሎትም በሀሳብም እንዲሁም ሁሉ አቀፍ ድጋፍ ያደረጋችሁና እያደረጋችሁ ያላችሁ ግለሰቦችና ባለድርሻ አካላት ባጠቃላይ በቅርብም በሩቅም ያላችሁ የመቱ ዩኒቨርሲቲ ወዳጆች ለ10ኛ ዓመት በዓላችን እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡
ክቡራትና ክቡራን የመቱ ዩኒቨርሲቲ ቤተሰቦች፤ ያለፉት አስር አመታት ለዩኒቨርሲቲያችን የጊዜ ዑደቶችና ሽግግሮች ልኬት ብቻ የሚታይ አይደለም፡፡ እንደ ተቋማችን እነዚህ ዓመታት አስር ቆጥረን የልደት ሻማችንን የምናበራበት ሳይሆን ዩኒቨርሲቲያችን የዛሬ 10 ዓመት ገደማ ከሀሳብ ጥንስስነት አልፎ የመጀመሪያዋን የማዕዘን ድንጋይ ከተቀመጠበት ጊዜ እንስቶ ውብና ማራኪ የሆነ ግቢ እስገነባንበት፤ በጥቂት መምህራንና የአስተዳደር ስራተኞች 300 የማይሞሉ ተማሪዎችን ተቀብለን አንድ ብለን የመማር ማስተማሩን ከጀመርንበት ጊዜ ጀምሮ በአሁን ሰዓት ከ26000 በላይ ተማሪዎችን በሁለት ካምፓሶች፣ በሰባት ኮሌጆችና ትምህርት ቤቶች በተለያዩ መርህ ግብሮች የማስተማር አቅም እስከ ገነባንበት ድረስ፤ አንድም ቤተ ሙከራና ወርክሾፖች ባልነበሩበት ጊዜ አንስቶ ከ40 በላይ የተደራጀ የልምምድ ቤተ መከራዎችን እስከገነባንበት፤ አንድ የማጣቀሽ መፅሀፎ ከሌለበት አንስቶ በአሁን ስዓት የተደራጀና የዘመኑ ቤተ መፅህፎቶችን እስካደራጀንበት፤ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር አድርገን በማህበረሰብ አገልግሎት ማህበረስባችን ዘርፈ ብዙ ተጠቃሚ ያደርግንበትን ሂደትና ሌሎች ስኬቶችን ያካተተ የ10 ዓመታት ጉዞ ነው፡፡
ዛሬ 10ኛ ዓመታችንን ስናከብር ሁሉም ነገር በስኬት የደመቀና አልጋ ባልጋ የሆነ እንዳልነበር እሙን ነው፡፡ ለጉዞአችን ስኬቶች እንዳጋጠሙን ሁሉ በተጻጻሪው ብዙ ተግደሮቶችና ችግሮች አጋጥመውናል፡፡ ለእነዚህም ችግሮች እጅ ሳንስጥ በትጋት በመስራት ዛሬ ላይ ደርስናል፡፡ በዚህ ሂደቶች ውስጥ ከዚህ በፊት በተለያዩ ጊዜያት የነበሩት አመራሮችና የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ ለሰሩት ስራ እውቅና መስጠት ግድ ይላል፡፡ ዛሬ ለደረስንበት ተቋማዊ ቁመና እነሱ በጣሉት መሰረት ላይ ተጨማሪ ስራዎችን በመስራት ነው፡፡ ምክንያቱም የተቋም ግምባታ ቅብብሎሽ ስለሆነ የትላንቱን ማስቀጠልና የቡድን ስራም መስረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ለነበራችሁና አሁንም ላለችሁት ምስጋናዬን በመቱ ዩኒቨርሲቲና በራሴ ስም ልጋልፅላችሁ እወደለሁ፡፡
ክቡራትና ክቡራን
እንደ ተቋም ገና ጉዞ ጀመረን እንጂ መዳራሻችን ሩቅ ነው፡፡ ትላንት ብዙ መልካምና ድንቅ ስራዋችን አሳክተናል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥም ችግሮችና ተግደሮቶችም አጋጥመውናል፡፡ ነገር ግን ትላንት ጥሩ ስርተናል ብለን መኩራራት የለብንም፡፡ ምክንያቱም ጅማሮ ላይ ነን እንጂ ከእቅዳችን አንጻር አልመን ከተነሳነው ግባችን ለመድረስ ገና ብዙ ትጋትና ጥንካሬ ይጠበቅብናል፡፡ ይህንንም ትጋትና ጥንኬሬ ያለፉትን ስኬቶቻችንን በመቀመር እንዲሁም ካጋጠሙን ችግሮችና ተግደሮቶችንን ደግም ልምድና ትምህርት በመቅስም ለተሻለ ስራና ስኬት መዘጋጀት ይኖርብናል፡፡
በመጨረሻም በድጋሚ እንኳን አደረሴችሁ እያልኩ በቀጣይ የዩኒቨርሲቲያችንን ተልዕኮና ራዕይ ስኬት በትብብርና በቡድን ሰሜት እንድንተጋ አደራ እላለሁ፡፡
ዶ/ር እንደገና አበበ ገምታ
ፕሬዝዳንት
Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.