በመቱ ዩኒቨርሲቲ በ2013 ዓ.ም የሁለተኛ ዲግሪ ለመማር ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ መቱ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን ተቀብሎ በመደበኛ (Regular) እና በእረፍት ቀናት (Weekend) ለማስተማር ባወጣዉ ማስታወቂያ መሰረት የመግቢያ ፈተና ለመዉሰድ በመጠባበቅ ላይ ያላችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው ጥቅምት 10/2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ላይ ስለሆነ ተፈታኞች በዕለቱ ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በዩኒቨርሲቲዉ ቅጥር ግቢ በመገኘት የመግቢያ ፈተናውን እንድትወስዱ እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ:

  • በደሌ ላይ የተመዘገባችሁ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቦታ ፡- በደሌ ከተማ ለምለም ካርል 1ኛ ደረጃ ት/ቤት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  • የባንክ ኦሪጅናል ደረሰኝ (Original bank receipt) ያላቀረባችሁ አመልካቾች ለፈተና ስትመጡ ኦሪጅናል ደረሰኙን ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
    የመቱ ዩኒቨርሲቲ ድህረ-ምረቃ ት/ቤት

Post expires at 2:33pm on Wednesday October 21st, 2020