የተማሪዎች ጥሪ ማስታወቂያ
 Posted On: Oct 08, 2026

Announcement

 

በ2019 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ መቱ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች (Freshman) እና በ2018 ዓ.ም በመቱ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የአገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች፤ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚካሄደው ጥቅምት 9 እና 10/2019 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ እያሳሰብን፣ ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን። 

ማሳሰቢያ 

  • በ2018 ዓ.ም. በበደሌ ካምፓስ በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁና በ2019 ዓ.ም. በትምህርት ሚኒስቴር ተመድባችሁ ስማችሁ በፊደል A-B የሚጀምር የተፈጥሮ ሳይንስና የማኅበራዊ ሳይንስ ስትሪም ተማሪዎች፣ ምዝገባችሁ የሚካሄደው በበደሌ ካምፓስ መሆኑን እናሳስባለን። 
  • የሌሎች ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው በዋናው ግቢ ይሆናል። 

ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ 

Ø  ብርድ ልብስ፣ አንሶላና የትራስ ልብስ፣ 

Ø  የስፖርት ልብስ፣ 

Ø  ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች ኦሪጅናልና ኮፒ፣ 

Ø  ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda National ID)፣ 

Ø    መጠኑ 3x4 የሆነ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ  ይዛችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን። 

 

                                                                         የመቱ ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጅስትራር ጽ/ቤት 

© 2026 Mattu University. All Rights Reserved.