መቱ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት 27/9/2013 ዓ.ም መቱ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ ከኢሉ አባበር ዞን ወረዳዎች ለተወጣጡ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ፈጠራ ስልጠና ተሰጠ፡፡ የስራ ፈጠራ ስልጠናው የተሰጠው የተለያዩ ከኢሉ አባበር ዞን ወረዳዎች ለተወጣጡ ስራ አጥ ለሆኑ ወጣቶች ነው፡፡ ሰልጣኝ ወጣቶች ከስልጠናው ባገኙት ክህሎት የራሳቸው ስራ ፈጥረው መስራት ይችላሉ፡፡ ሰልጣኝ ወጣቶችRead More →

የህዝብና ውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ሰኔ 21/2013 ዓ.ም መቱ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢዉን የወተትና ስጋ ምርት ለማሻሻል የዳልጋ ከብት ማዳቀል መርሀ ግብር ኢሉ አባቦር ዞን በመቱ ወረዳ በአሌ ቡያ ቀበሌ በይፋ አስጀመረ፡፡ መቱ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢዉን የወተትና ስጋ ምርት ለማሻሻል የዳልጋ ከብት ማዳቀል መርሀ ግብር ኢሉ አባቦር ዞን በአሌ ቡያ ቀበሌ በይፋ አስጀመረ፡፡ ፕሮጄክቱ በዞኑ የተጀመረዉ በመቱ ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪነት በአሌ ቡያ ቀበሌ ነዉ፡፡ ይህንን ፕሮጄክት ያስጀመሩት ዶ/ር ኦዳ ግዛዉ ባስተላለፉት መልዕክትም ፕሮጄክቱ በአካባቢዉ የሚገኙ ከብቶች የወተትና ስጋ ምርትን ለማሻሻል ታስቦ የተጀመረ ሲሆን ይህንን ስራ ለመስራት በዋናነት በዩኒቨርሲያችን አስተባባሪነት ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል መንግስት፣ የኢኖቨሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር እንዲሁም ከጂማ፣ ወለጋና አምቦ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በትብብር ይህንን በቴክኖሎጂ የታገዘ የክብቶች የማዳቀል ስራ በምዕራብ ኦሮሚያ ይሰራል ብለዋል፡፡ ይህ የከብቶች የወተትና ስጋ ምርት ማሻሻል ፕሮጄክት በቡኖ በደሌና ኢሉአባቦር ዞኖች በሚገኙ ወረዳዎች ስር ባሉ ቀበሌዎች ይህንን በወተትና ስጋ ምርት የተሻሉ ተብለዉ በጥናት በተለዩ ቀበሌች ሲሆን በቀጣይ አምስት አመታት በሁለቱ ዞኖች ሁሉም ወረዳዎችና ቀበሌዎች ለማዳረስ እቅድ መያዙንም ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲዉ የምርምር፤ ማህበረሰብ አገልግሎትና ትስስርና ትብብር ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር በድሉ ተካ በመርሃ ግብር ላይ ባስተላለፉት መልእክት ሀገራችን በቀንድ ከብት ቁጥር ከመጀመሪያዎቹ ብትመደብም በወተትና ስጋ ምርት ወደኋላ የቀረች ሀገር በመሆኗ የከብቶችን የወተትና ስጋ ምርት ለማሻሻል በሳይንሳዊ አሰራር በቴክኖጂ የታገዘ የማዳቀል ስራ መጀመራችን ለአካባቢዉ አርሶ አደር ትልቅ ስኬት ነዉ ብለዋል፡፡ የማዳቀል ስራው ላይ ተሳተፉ ባለሙያዎች የአሌ ቡያ ቀበሌ የእንስሳት ባለሙያ እንደተናገሩት በዩኒቨርሲቲ ዉስጥ ካገኘነው የተግባር ልምምድ በተጨማሪ አሁን በመቱ ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪነት የአጭር ጊዜ ተጨማሪ ስልጠና የተሰጠን በተጨባጭ ይህንን የማዳቀል ቴክኖሎጂ ስራ ላይ እንድናዉል አግዞናል ብለዋል፡፡ ስለሆም ዩኒቨርሲቲዉ የጀመረዉን አበረታች ስራ በቀጣይም የህብረተሰቡን ችግር ፈቺ የሆኑ ሌሎች ተመሳሳይ ስራዎች መስራት አለበት ብለዋል፡፡ የፕሮጄክቱ ተጠቃሚ የሆኑ አርሶ አደሮች በሰጡት አስተያየት የፕሮጄክቱ ተጠቃሚ በመሆናቻዉ መደሰታቸዉን ገልጸዉ በቀጣይም ዩኒቨርሲቲዉ ተመሳሳይ ስራዎችን ለህብረተሰቡ እንዲሰራ ጠቁመዋል፡፡ በአጠቃላይ ይህ የከብቶች የወተትና ስጋ ምርትን ለማሻሻል የማዳቀል ፕሮጄክት በተመሳሳይ መልኩ የማዳቀል ስራ በቅርቡ በቡኖ በደሌ ዞን በደሌ ወረዳ መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን በዚህ መርሃ ግብር በሁለቱም ዞን ሁለት ሺህ የሚሆኑ ላሞች በዚህ ቴክኖሎጂም ይዳቀላሉ ተብሏል፡፡Read More →