የህዝብና ውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት 26/02/2014 ዓ. ም መቱ ዩኒቨርሲቲ በጎሬ ከተማ ያሰራውን የተቀናጀ የከተማ ግብርና የአትክልትና የዶሮ እርባታ ፕሮጀክት ለተጠቃሚዎች አስተላለፈ፡፡ ፕሮጀክቱ የተሰራው በመቱ ዩኒቨርሲቲ ተማራማሪዎች ሲሆን የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው ሴቶች ኑሮ ለማሻሻልና ለመደገፍ ተብሎ የተሰራ ነው፡፡ የተቀናጀ የቴክኖሎጂ የከተማ ግብርና በውስጡ በትንሽ ቦታ ላይ የአትክልትና የዶሮ ዕርባታ ያካተተ ነው፡፡Read More →