In accordance with the revised proclamation No.433/2005 for the establishment of the Federal Ethics and Anti-corruption commission, Ethics and Anti-corruption Directorate of Mettu University established in 2014 E.C. The Directorate is accountable to the President.

Vision of the Directorate

To become one of the best Anti-Corruption higher education institutions in Ethiopia in 2025 by curbing corruption to the level where it cannot become an obstacle to good governance and development efforts of the country.

Mission of the Directorate

In co-operation with relevant bodies to ensure transparency and accountability in the institution by promoting ethics and anti-corruption education, mobilizing employees against corruption, conducting assets registration and disclosure undertakings and preventing corruption and impropriety.

Core values of the Directorate

  1. Responsibility and Accountability
  2. Exemplary
  3. Transparency
  4. Honesty
  5. Participatory
  6. Supremacy of the law
  7. Working together

Objectives of the Directorate

  1. In cooperation with relevant bodies to strive to create an aware employee where corruption will not be conducted or tolerated by promoting ethics and anti-corruption education.
  2. In cooperation with relevant bodies to prevent corruption offences and other improprieties.
  3. To expose, investigate and prosecute corruption offences and impropriety.

Powers and Duties of the Directorate

  1. In cooperation with relevant bodies to combat corruption and other impropriety by creating awareness through educating the employees about the effects of corruption and the promotion of ethics in the institution.
  2. In accordance with the relevant bodies, to prevent corruption by studying or causing to be studied the practice and procedures in the institution to secure the revision of methods as specified by law. of work which may be conducive to corrupt practices as well as follow up their implementations; and inform or remind essential, to take proper measures or give decision, and advise or assist on same, upon request, any other persons.
  3. To investigate or cause the investigation of any complaints of alleged or suspected serious breaches of codes of ethics in the institution, and follow the taking of proper measures.
  4. In cooperation with relevant bodies to register or cause the registration of assets and financial interests of public officials and other public employees compellable to do so.         

Address of Ethics and Anti-Corruption Directorate

Tell. 047 841 6320

Email: ethcor@meu.edu.et

የመቱ ዩኒቨርሲቲ የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት

በተሻሻለዉ የፌደራል የሥነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 333/1997 መሠረት የመቱ ዩኒቨርሲቲ የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት በ2006 ዓ.ም ተቋቋመ፡፡ የዳይሬክቶሬቱ ተጠሪነትም ለዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ነዉ፡፡

የዳይሬክቶሬቱ ራዕይ

በ2017 ሙስና እና ብልሹ አሰራር ለልማትና መልካም አስተዳደር እንቅፋት ከማይሆንበት ደረጃ በማድረስ በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ከሆኑ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንዱ መሆን

የዳይሬክቶሬቱ ተልዕኮ

አግባብነት ካላቸዉ አካላት ጋር በመተባበር የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ትምህርትና ሥልጠና በማስፋፋት ለጸረ ሙስና ትግል የተደራጀ የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር፣የሚመለከታቸዉን የመንግሥት አካላት ሃብት በመመዝገብ ማሳወቅ፣ሙስናና ብልሹ አሰራርን በመከላከል የመንግሥት አሰራሮች ላይ ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ማድረግ

የዳይሬክቶሬቱ እሴቶች

  1. ኃላፊነትና ተጠያቂነት
  2. አርኣያነት
  3. ግልጽነት
  4. ታማኝነትና በዕዉቀት ላይ የተመሠረተ አገልግሎት
  5. አሳታፊነት
  6. የህግ የበላይነት
  7. በጋራ መሥራት

የዳይሬክቶሬቱ ዓላማዎች

  1. ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመተባበር ሠራኛዉን በጸረ ሙስና ትምህርቶች፣ በሥራ ዲሲፕሊን፣በሙያ ስነ ምግባር፣በህዝብ አገልጋይነትና በኃላፊነት ስሜት በማነጽ የነቃና ሙስናን ሊሸከም የማይችል ሠራተኛ እንዲፈጠር ጥረት ማድረግ
  • ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመተባበር በተቋሙ የሙስና ወንጀልንና ብልሹ አሰራርን መከላከል
  • የሙስና ወንጀልና ብልሹ አሰራር እነዲጋለጥ፣እንዲመmረመርና በአጥፊዎች ላይ ተገቢዉ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ

የዳይሬክቶሬቱ ሥልጣንና ተግባር

  1. አግባብነት ካላቸዉ አካላት ጋር በመተባበር ስለሙስና ጎጂነት የሠራተኛዉ ንቃተ ህሊና እንዲጎለብት በማስተማር እና መልካም ስነ ምግባር በህዝብ አገልግሎት ዉስጥ እንዲስፋፋ በማድረግ ሙስናና ብልሹ አሰራርን መዋጋት
  • አግባብነት ካላቸዉ አካላት ጋር በመተባበር በተቋሙ ዉስጥ ለሙስናና ብልሹ አሰራር የተጋለጡና ሊጋለጡ የሚችሉ የአሰራር ሥርዓቶችን በማጥናት ወይም እንዲጠኑ በማድረግ እንዲሻሻሉ ማማከርና ማሳሰብ፣የአሰራር ሥርዓቶቹ የተሻሻሉ መሆናቸዉን መከታተል እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ተገቢ የሆነዉ  እርምጃ እንዲወwሰድ ወይም ዉሳኔ እንዲሰጥ አግባብ ላለዉ አካል በማሳወቅ ወይም በማሳሰብ ሙስናን የመከላከል፣ በሌሎች ሲጠየቅ ተመሳሳይ ምክርና ድጋፍ መስጠት
  • በተቋሙ ዉስጥ ከባድ የስነ ምግባር መጣስ ስለመፈጸሙ ወይም ጥርጣሬ ሲኖረዉ የማጣራት ወይም እንዲጣራ የማድረግ እና ተገቢዉ እርምጃ እንዲወሰድ የመከላከል
  • አግባብነት ካላቸዉ አካላት ጋር በህግ በሚደነገገዉ መሠረት የመንግሥት ባለሥልጣኖችን እና በህግ ሀብታቸዉንና የገንዘብ ጥቅማቸዉን እንዲያስመዘግቡ ግዴታ ያለባቸዉን የመንግሥት ሠራተኞች ሀብትና የህዝብ ጥቅሞች መዝግቦ የመያዝ ወይም ተመዝግበዉ እንዲያዙ የማድረግ  ናቸው፡፡

የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ዳሬክቶሬት አድራሻ

ስልክ 047 841 6320

ኢሜይል፡ ethcor@meu.edu.et