ማስታወቂያ

የመቱ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ በተሰጠው ስልጣን እና ኃላፊነት መሰረት በዩኒቨርሲቲው የቢዝነስ እና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት የሥራ ኃላፊነት መደብ ላይ ከመምህራን መካከል አወዳድሮ መመደብ ይፈልጋል፣

በመሆኑም በተጠቀሰው የኃላፊነት ቦታ ላይ የመወዳደሪያ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተወዳዳሮዎች አስፈላጊውን ማስረጃ በማቅረብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይገልጻል፡፡

የመወዳደሪያ መስፈርት እንደሚከተለው ይሆናል፡-

  1. ቢያንስ የፒ.ኤች.ዲ ወይንም ሁለተኛ ዲግሪ ከረዳት ፕሮፌሰርነት የትምህርት መዕረግ ጋር እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት
  2. በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ቢያንስ 2 ዓመት ያገለገለ/ች
  3. ለሥራ መደቡ አግባብነት ያለው የአመራርነት ልምድ ያለው/ያላት
  4. ከፍተኛ የስራ ተነሳሽነትና የሙያ ስነ-ምግባር ያለው/ያላት
  5. በተቋሙ የዘርፉን ተግባራት ለማሳካት የሚያግዝ ንድፈ ሃሳብ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
  6. በማስተማር፣ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ልምድ ያለው/ያላት

የምዝገባ ቦታ

  • በዋናው ግቢ፣ አዲሱ የአስተዳደር ህንጻ፣ ሶስተኛ ፎቅ፣ የፕሬዚዳንት አማካሪ ቢሮ ዘውትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ ፡-

  • ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ

የመቱ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስ እና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት ዕጩ አስመራጭ ኮሚቴ

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.