ቀን 02/10/2013ዓ.ም
ማስታወቂያ
የመቱ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ቦርድ በተሰጠው ስልጣንና ሃላፊነት መሰረት በዩኒቨርሲቲው የምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎት፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ትስስር ምክትል ፕሬዚዳንት የሥራ ኃላፊነት መደብ ላይ ከመምህራን መካከል አወዳድሮ መመደብ ይፈልጋል፣
በመሆኑም በተጠቀሰው የሃላፊነት ቦታ ላይ የመወዳደሪያ መስፈርቶቹን የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች አስፈላጊውን ማስረጃ በማቅረብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይገልጻል፡፡
የመወዳደሪያ መስፈርት እንደሚከተለው ይሆናል፡
1. ቢያንስ የፒ.ኤች.ዲ ወይንም ሁለተኛ ዲግሪ እና ረዳት.
ፕሮፌሰር የትምህርት ማዕረግ ያለው/ያላት
2. በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ቢያንስ 2 ዓመት ያገለገለች
3. ከተጠቀሱት የሃላፊነት ቦታዎች ጋር ተያያዥነት ባላቸው.
የስራ መደቦች ላይ ልምድ ያለው/ያላት
4. ከፍተኛ የስራ ተነሣሽነትና የሙያ ስነምግባር ያለው/ያላት
5. የተቋሙን ራዕይ ለማሳካት የሚያግዝ ንድፈ ሃሳብ
ማቅረብ የሚችል/የምትችል
6. የምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ተሳትፎ ያለው/ያላት
የምዝገባ ቦታ
በዋናው ግቢ፣ አዲሱ የአስተዳደር ህንጻ፣ ሶስተኛ ፎቅ፣ የፕሬዚዳንት አማካሪ ቢሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት
ማሳሰቢያ ፡• ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ
የመቱ ዩኒቨርሲቲ የምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎት፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ትስስር ምክትል ፕሬዚዳንት ዕጩ አስመራጭ ኮሚቴ

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.