Public and External Relations Directorate
June 24/2021

Mettu University Registrar Directorate is providing training for teachers and Registrar workers

Mettu University Registrar Directorate is providing training to teachers on the Academic Registrar Rules and regulations, new college structure, Higher Education Proclamation 1152/2019, and SRS.

In his opening remarks, Dr. Leta Deresa, Academic Vice President of the University, said that the university is preparing to receive new students assigned to the university in 2013 by the Ministry of Science and Higher Education therefore this training will help teachers to support students adequately to ensure equitable teaching and learning.

Dr. Diriba Gemechu, Registrar Director of the University, who is providing training, said that such trainings are aimed at supporting teachers on the rules and regulations that are being issued and amended.

ህዝብና ውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ሰኔ 17/2013 ዓ.ም
መቱ ዩኒቨርሲቲ የሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት ለመምህራንና ለሬጅስትራር ሰራተኞች ስልጠና ሠጠ።
የመቱ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትር ዳይሬክቶሬት በዩኒቨርሲቲው በማስተማር ላሉት መምህራን በትምህርት ምዝገባ ህጎችና ደንቦች፣ በአጠቃላይ አዲስ የኮሌጅ አወቃቀር ፣ የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ 1152/2019 እና የተማሪዎች የምዝገባ ሲሰተም ላይ ለመምህራንና ለሬጅስትራር ሰራተኞች ስልጠና ሰጠ፡፡
መርሃ ግብሩን የመከፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው አካሚክ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ለታ ዴሬሳ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው በ2013 ዓ.ም በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ወደ ዩኒቨርሲቲው አዲስ የተመደቡ ተማሪዎችን ለመቀበል በዝግጅት ላይ እንደመሆኑ መጠን ይህ ስልጠና ለመምህራን በአዲሱ የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ 1152/2019 ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እንዲሁም ፍትሃዊ የመማር ማስተማር እንዲኖር ተማሪዎችን በበቂ ሁኔታ ለማገዝ ይረዳል ብለዋል፡፡
ስልጠናውን ለመህምራን በመስጠት ላይ የሚገኙት የዩኒቨርሲቲው ሬጅትራር ዳይሬክቶሬት ዶ/ር ድሪባ ገመቹ እንደተናገሩት መሰል ስልጠናዎች በየጊዜው በሚወጡ እና በሚሻሻሉ ህጎችና ደንቦች ዙሪያ ላይ መምህራን ግንዛቤ እንዲኖራቸው የሚሰጡ መሆናቸውን ጠቅሰው አሁን እየተሰጠ ያለውም ይኸን በመደገፍ በአካደሚክ ምዝገባ ህግችና ደንቦች እንዲሁም በተማሪዎች የምዝገባ ዘዴ ላይ እንደሚያተኩር ገልፀዋል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.