መቱ ዩኒቨርሲቲ ከባለድርሻ አካላት ጋር የአካዳሚክ ምክክር መድረክ አካሄደ፡፡ የአካዳሚክ ምክክር መድረኩ የተካሄደው ከኢሉአባቦርና ቡኖ በደሌ ዞኖች ተወላጅ ምሁራን፣ ባለሀብቶችና በመንግስት ኃላፊነት ቦታዎች ላይ ካሉት ባለድርሻ አካላት ጋር ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው የምክክር መድረኩን ያካሄደው መቱ ዩኒቨርሲቲን በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ካሉት ተቋማት ጋር ለማስተሳሰር እነዚህ ባለድርሻ አካላት ያለቸው ሚና ጉልህ መሆኑና በዚህ ረገድ ከዩኒቨርሲቲው ጎን በመሆን እንዲሰሩ ታሰቦ ነው፡፡ በምክከር መድረኩ ላይ መቱ ዩኒቨርሲቲ ከምስረታ ጅምሩ አንስቶ የተሰሩ ስራዎች የቀረበ ሲሆን በቀጣይ እነዚህ ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸው አስተዋጽኦም አስቀምጠዋል፡፡ በዚሁ መሰረት ዩኒቨርሲቲውን በማስተዋወቅና ግንኙነት በመፍጠር ረገድ አጠናክሮ መስራት እንዳለባቸው፤ እንዲሁም በሚያስፈልገው ሁሉ ላመገዝ ከመግባባት ላይ ተደርሰዋል፡፡ በምክክር መድረኩ ላይ የዩኒቨርሲቲው ቦርድ አባል ኢ/ር ዘሪሁን ጌታነህና ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ምሁራን፣ በተለያዩ ጊዜያት ዩኒቨርሲቲው በአካባቢው እንድከፈት አስቋጽኦ ሲያደርጉ የነበሩ ታዋቂ ሰዎች፣ በመንግስት በተለያየ ኃላፊነት ላይና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ግለሰቦች ተግኝተዋል፡፡ 
በመጨረሻም ዩኒቨርሲቲው አሁን ካለበት የበለጠ በሁሉም መስኮች የተጣለበትን ኃላፊነቶች እንዲወጣና በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ካሉት የአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ለመስራት አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ አቋቁመዋል፡፡ የተቋቋመው ኮሚቴም ስራዎችን አቅዶና አፈጻጸሙን እየገመገመ እንዲሄድ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.